የባህል ወረራ ምንድነው?
የባህል ወረራ የራሱ የሆነ ጥቅምና ጉዳት አለው
የባህል ወረራ የሚኖረው ተጽዕኖ አንድ ማህበረሰብ አዲስ ባህል ለመቀበል ወይም ላለመቀበል ባለው ፍላጎት የሚወሰን ይሆናል
የባህል ወረራ ምንድነው?
የባህል ወረራ ምን ማለት ነው? ፤ ጥቅምና ጉዳቱስ ሜንድነው?
የባህል ወረራ የራሱ የሆነ ጥቅምና ጉዳት አለው።
ጥቅሞቹ፦
1) የባህል ልውውጥ- የባህል ወረራ አዲስ ሀሳብ፣ ልምድ እና አረዳድ እንዲመጣ እና የባህል ብዙሃነት እንዲፈጠር ያደርጋል
2) አዲስ ፈጠራ
ለተለያዩ ባህሎች ተጋላጭነት ሲኖር እንደ አርት፣ ሙዚቃ፣ የምግብ አሰራር እና ቴክኖሎጂ በመሳሰሉ ዘርፎች ፈጠራ እና መሻሻል ለማድረግ ያነሳሳል
3) የኢኮኖሚ እድገት
በቱሪዝም፣ በንግድ እና ሸቀጦችን እና አገልግሎቶችን በመቀያየር ኢኮኖሚን ለማነቃቃት ይጠቅማል
አሉታዊ ተጽዕኖው/ ጉዳቶቹ
1) የባህል ማንነትን ማጣት-የበላይ የነበሩ ባህሎች እንዲደበዝዙ ወይም እንዲሸረሸሩ በማድረግ የባህል ማንነትን እስከማሳጣት ሊያደርስ ይችላል
2)ማህበራዊ ቀውስ
አዲስ በሚመጣው እና በነባሩ ባህል መካከል በሚኖር አለመጣጣም ምክንያት ግጭት እንዲቀሰቀስ ያደርጋል
3) የኢኮኖሚ አመመጣጠን
የተወሰኑ ቡድኖች ከወረራው የበለጠ ተጠቃሚ ሲሆኑ በማህበረሰቡ ውስጥ የኢኮኖሚ አመመጣጠን ያመጣል
የባህል ወረራ የሚኖረው ተጽዕኖ አንድ ማህበረሰብ አዲስ ባህል ለመቀበል ወይም ላለመቀበል ባለው ፍላጎት የሚወሰን ይሆናል።