የጋምብያው ፕሬዝዳንት ታህሳስ ወር በሚካሄደው የሀገሪቱ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ እንደሚሳተፉ አስታወቁ
ፕሬዝዳንት ባሮው በምርጫው የህዝብ ውሳኔ እንደሚያደርጉም ከወዲሁ ተናግሯል
ባሮው የቀድሞው አምባገነን መሪ ጃሜህን በመተካት እንደፈረንጆቹ 2016 በትረ ስለጣን መጨበጣቸው ይታወቃል
የጋምብያው ፕሬዝዳንት አዳማ ባሮው በመጪው ታህሳስ 4/2021 በሚካሄደው የሀገሪቱ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ እንደሚሳተፉ አስታወቁ፡፡
ፕሬዝዳንቱ በቀጣዩ ምርጫ የመወዳደር ፍላጎት እንዳላቸው ይፋ ባደረጉበት ወቅት በሺዎች የሚቆጠሩ ደጋፊዎች በዋና ከተማይቱ ባንጁል ጎዳናዎች ተሰልፈው ለፕሬዝዳንቱ ያላቸው ድጋፍ ገልጸውላቸዋል፡፡
ትንሿና ምዕራብ አፍሪካዊቷ ሀገር በታህሳስ 4/2021 የምታካሂደው ምርጫ ከአምባገነኑ የቀድሞው ፕሬዝዳንት ያህያ ጃሜህ ከስልጣን መወገድ በኋላ፤ ለመጀመርያ ጊዜ የሚካሄድ እንደመሆኑ በሀገሪቱ ዴሞክራሲያዊ ሽግግር እውን ለማድረግ ወሳኝ ነው ተብሎለታል፡፡
እንደ ኤ.ኤፍ.ፒ ዘገባ "የጋምብያ ህዝቦች የመሰላቸውን ውሳኔ ቢወስኑም፤ የመጣውን ውጤት የማከብር ይሆናል ምክንያቱም እኔ ዴሞክራት ነኝ እንዲሁም በህግ የበላይነት እና ዴሞክራሲ አምናለው” ብሏል የ56 ዓመቱ ፕሬዝዳንት ባሮው፡፡
የቀድሞው መሪ ጃሜህ እንደፈረንጆቹ 1994 በትረ ስልጣን ሲቆጣጠሩ ካለ ምንም የደም መቃባት ነበር፡፡
ጃሜህ በትረ ስልጣኑን ከጨበጡ በኋላ አወዛጋቢ ምርጫ በማድረግ፤ እንደፈረንጆቹ 2016 በባሮው አስከተተኩበት ጊዜ ድረስ በስልጣን እንደቆዩም የሚታወቅ ነው፡፡
ጀሜህ ከስልጣን ለመልቀቅ በኋላም ወደ ኢኳተርያል ጊኒ ለመኮብለል ያስገደዳቸውም በሀገሪቱ ለስድስት ሳምታት የዘለቀና በወታደራዊ ጣልቃ ገብንት የታጀበ ቀውስ በመፈጠሩ ነው፡፡
የመብት ተሟጋቾች ጀሜህ በ22 አመቱ የስልጣን ዘመናቸው እጅግ ብዙ ወንጀሎችን ፈጽሟል እንዲሁም የሞት ቡድኖችን በመጠቀም እስከ አስገድዶ መድፈር እና የጠንቋዮች አደን የመሳሰሉ ወንጀሎች ስፖንሰር አድርጓል ብለው ይከስዋቿል፡፡
አሁን ላይ የባሮው ብሄራዊ የህዝብ ፓረቲ (NPP) ከጃሜህ የአርበኝነት ለውጥ እና ግንባታ ጥምረት (APRC) ፓርቲ ለምርጫው ጥምረት ፈጥረዋል መባሉም የመብት ተሟጋቾች ኩፉኛ እየተቹት ይገኛሉ፡፡
በጋምብያ ምርጫ 19 እጩዎች ለፕሬዝዳንትንት ለመወዳደር መመዝገባቸው የሀገሪቱ የምርጫ ኮሚሽን አስታውቋል፡፡እጩዎቹ ከህዳር 9/2021 ጀምሮ የምርጫ ቅስቀሳ ማድረግ እንደሚጀምሩ ተገልጿል፡፡