የኮሮና ቫይረስን ማከም የሚያስችል የእንክብል መድሃኒት ተዘጋጀ
እንግሊዝ አስቀድማ 480 ሺህ መጠን ያለው መድሃኒት ለመግዛት አስቀድማ ጠይቃለች
እንግሊዝ አስቀድማ 480 ሺህ መጠን ያለው መድሃኒት ለመግዛት አስቀድማ ጠይቃለች
የኮሮና ቫይረስን ማከም የሚያስችል እንክብል መድሃኒት በአሜሪካን ሀገር ተገለጸ ፡፡
በአሜሪካው መርክ መድሃኒት አምራች ኩባንያ እንደተዘጋጀ የተገለጸው ይህ ‘ማልኑፒራቪር’ የተሰኘው እንክብል መድሀኒት መጀመሪያ ላይ ጉንፋንን ለማከም ነበር የተዘጋጀው፡፡
ይሁንና አሁን ላይ በተደረገለት ማሻሻያ መሰረት ለኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎች የተዘጋጀ ሲሆን የእንግሊዝ መድሀኒት ተቆጣጣሪ ተቋም መድሀኒቱ ለታማሚዎች እንዲሰጥ ፈቃድ ሰጥተዋል፡፡
እንደ ቢቢሲ ዘገባ ከሆነ መድሃኒቱ በኮሮና ቫይረስ ለተጠቁ እና ተጋላጭ ለሆኑ ሰዎች በቀን ሁለት እንክብል እንዲወስዱ በሀኪሞች ይታዘዛል ተብሏል፡፡
መድሃኒቱ በጉንፋን እና ኮሮና ቫይረስ ተጠቅተው ወደ ሆስፒታል የሚገቡ እና የሚሞቱ ሰዎችን በግማሽ እንደሚቀንስ ታምኖበታል፡፡የእንግሊዝ ጤና ሚኒስትር ሳጂድ ጃቪድ እንዳሉት መድሀኒቱ ጨዋታ ቀያሪ ነው ያሉ ሲሆን መድሃኒቱ ይፋ የተደረገበት ቀንም ታሪካዊ መሆኑን አክለዋል፡፡
‘ማልኑፒራቪር የተሰኘው ይህ የእንክብል መድሃኒት በአሜሪካው መርክ መድሃኒት አምራች ኩባንያ እና በእንግሊዙ ሪጅባክ ባዮቴራፒቲከሰ ጥምረት በመመረት ኮሮና ቫየረስን በእንክብል መድሃኒት መልክ የጠዘጋጀው የመጀመሪያው ነው ተብሏል፡፡
ይህ መድሃኒት በሰውነታችን ውስጥ ያለ ኢንዛይም የኮሮና ቫይረስ ራሱና በማባዛት የቫይረሱና ተፈጥሯዊ ስሪት በማዛባት ቫይረሱ ጉዳት እንዳያደርስ የሚያደርግ መሆኑ ተገልጿል፡፡
ይህ መድሃኒት አሁን ላይ ለኮቪድ ተጋላጭ ከሆኑ እና ተጓዳኝ ህመም ላለባቸው ሰዎች መሰጠት እንደሚችል የእንግሊዝ መድሀኒት ቁጥጥር ባለስልጣን ዕውቅና ሰጥቷል ተብሏል፡፡
እንግሊዝ 480 ሺህ መጠን ያለው የ‘ማልኑፒራቪር እንክብል መድሃኒት አስቀድማ ያዘዘች ሲሆን የአሜሪካው ፋይዘር መድሃኒት አምራች ኩባንያ ደግሞ 250 ሺህ መጠን ያለው መድሃኒት በማምረት ላይ መሆኑ ተገልጿል፡፡