ጋሪ ሊንከን በቢቢሲ ላይ ሆስት እንዳያደርግ በሀገሪቱ መንግስት እገዳ ተጣለበት
ኢያን ራይትን ጨምሮ ሌሎች ታዋቂ የእንግሊዝ የቀድሞ ተጫዋቾች ውሳኔውን በመቃወም ስራ አቁመዋል
ታዋቂው የቀድሞ የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን ተጫዋች እና አምበል የሀገሪቱን መንግስት ተችተሃል በሚል መታገዱ ተገልጿል
ጋሪ ሊንከን በቢቢሲ ላይ ሆስት እንዳያደርግ በሀገሪቱ መንግስት እገዳ ተጣለበት።
ላለፉት 20 ዓመታት በእግር ኳስ ተንታኝነት እና በአቅራቢነት ሲሰራ የቆየው እንግሊዛዊው ጋሪ ሊንከር ከቢቢሲ ስፖርት አቅራቢነት እና ተንታኝነቱ ታግዷል።
ቢቢሲ ጋሪ ሊንከንን ከስራ ያገደው በጠቅላይ ሚኒስትር ሪሺ ሱናክ የሚመራው የብሪታንያ መንግስት ያወጣውን የስደተኞች ፖሊሲን መተቸቱን ተከትሎ ነው።
ብሪታንያ በአነስተኛ ጀልባዎች ወደ ግዛቷ የሚገቡ ስደተኞችን ወደ መጡበት ሀገር አልያም ወደ ሌላ ሶስተኛ ሀገር ለመመለስ የሚፈቅድ ህግ ማውጣቷን ተከትሎ ነው።
ጋሪ ሊንከን ይህ የብሪታንያ ህግ በመቃወም በትዊተር ገጹ ላይ መተቸቱን ተከትሎ ላለፉት በርካታ ዓመታት በተለይም “ማች ኦፍ ዘ ዴይ“ የሚባለውን የእግር ኳስ ፕሮግራም እንዳያዘጋጅ እና እንዳያቀርብ ከቢቢሲ ታግዷል።
ጋሪ ሊንከን የብሪታንያ መንግስትን ከናዚ ስርዓት ጋር በማነጻጸር ከለላ እና ድጋፍ ፈልገው በሚመጡ ዜጎች ላይ ያልተገባ ድርጊት እንዲፈጸምባቸው የሚያደርግ ነው ሲል ተችቷል።
ቢቢሲ ጋሪ ሊንከርን ከአቅራቢነት እና አዘጋጅነት ማገዱን ተከትሎ የዚህ ፕሮግራም አካል የሆኑት የቀድሞው የብሄራዊ ቡድን አጋሩ እና የአርሰናል አጥቂ የነበረው ኢያን ራይት ከስራው ራሱን አግሏል።
ከኢያን ራይት በተጨማሪም ሌላኛው የስራ አጋሩ ስቲቭ ዊልሰን እና ሌሎች የስራ ባልደረቦች የቢቢሲን ውሳኔ በመቃወም ስራቸውን እንደማይቀጥሉ አሳውቀዋል ተብሏል።
እገዳውን ያስተላለፈው ቢቢሲ በበኩሉ ስለ እገዳው እና ሌሎች እርምጃዎች በቀጣይ እንደሚያሳውቅ አስታውቋል።