ከተገደለችው እናቷ ማህጸን በህይወት የወጣችው ህጻን ህይወቷ አለፈ
ስድስት ወራትን ባስቆጠረው የእስራኤል እና ሀማስ ጦርነት የተገደሉ ፍልስጤማውያን ቁጥር ከ34ሺ ማለፉን የጋዛ ባለስልጣናት ተናግረዋል
በእስራኤል የአየር ጥቃት ከተገደለችው እናቷ ማህፈን በህይወት የወጣችው የጋዛዋ ህጻን የተወሰነ ቀናት ከቆነች በኋላ ህይወቷ አለፈ
በእስራኤል የአየር ጥቃት ከተገደለችው እናቷ ማህፈን በህይወት የወጣችው የጋዛዋ ህጻን የተወሰነ ቀናት ከቆነች በኋላ ህይወቷ ማለፉን ሲንከባከቧት የነበሩት ዶክተር በዛሬው እለት ተናገሩ።
ህጻኗ ሳብሪን አል ሮህ የሚል ስም ተሰጥቷት ነበር። ሮህ ማለት በአረብኛ ቋንቋ "ነፍስ" ማለት ነው።
እናቷ ሳብሪን አል ሳካኒ እስራኤል ባለፈው ቅዳሜ በጋዛ ደቡብዊ ጫፍ በምትገኘው ራፋ ከተማ በሚገኘው የቤተሰቦቿ ቤት ላይ ባደረሰችው የአየር ጥቃት ክፉኛ ቆሰለች።
በጦቃቱ ባለቤቷ ሽኩሪ እና የሶስት አመት ሴት ልጇ ማሌክ ተገደሉ።
የ30 ወራት ነፍሰጡር የሆነችው ሳብሪን አል ሳካኒ በራፋ ወደሚገኘው የኢምሬትስ ሆስፒታል በፍጥነት ተወሰደች። የደረሰባት ጉዳት ከባድ በመሆኑ እሷ ህይወቷ አለፈ፤ ነገርግን ዶክተሮች በሲሰራን ሴክሽን ህጻኗን ከማህጸኗ በህይወት አወጧት።
ይሁን እንጂ ህጻኗ የመተንፈሻ አካሏ ችግር እንዳጋጠማት እና በሽታ የመከላከል አቅሟም ደካማ እንደነበር ህጻኗን ሲከታተሉ የነበሩት በኢምሬትስ ሆስፒታል ዩኒት ኃላፊ ዶክተር መሀመድ ሰላማ ተናግረዋል።
ህጻኗ ህይወቷ ያለፈው በትናንትናው እለት ሲሆን አካሏ በራፋ በሚገኘው አሸዋማ መካነመቃብር አርፏል።
"እኔ እና ሌሎች ዶክተሮች ህይወቷን ለማዳን ጥረት አድርገን ነበር፤ ነገርግን ህይወቷ አለፈ። ለእኔ በግሌ ከባድ እና የሚያም ቀን ነበር" ሲሉ ዶክተር ሰላማ ለሮይተርስ ተናግረዋል።
ዶክተር ሰላማ እንደገለጹት ህጻኗ የተወለደችው የመተንፈሻ አካሏ ሳይጠነክር እና በሽታ የመከላከል ደካማ ሳለ ነበር።
ዶክተር ሰላማ "(የሳብሪን አል ሮህ) አያት ሮህ የእኗቷ፣ የአባቷ እና የህቷን ማስወሻ በህይወት የምታቆየው እሷ በመሆኗ እንድንከባከባት አሳስበውኝ ነበር፤ ነገርግን የፈጣሪ ፈቃድ ሆኖ ህይወቷ አለፈ" ይላሉ።
ስድስት ወራትን ባስቆጠረው የእስራኤል እና ሀማስ ጦርነት በአብዛኛው ሴቶች እና ህጻናት ጨምሮ የተገደሉ ፍልስጤማውያን ቁጥር ከ34ሺ ማለፉን የጋዛ ባለስልጣናት ተናግረዋል።
እስራኤል የሀማስ ታጣቂዎችን ለማጥፋት እያደካሄደች ባለው ዘመቻ ንጹሀንን ኢላማ ማድረጓን አስተባብላለች።
አብዛኛው የጋዛ ህንጻዎች እስራኤል በፈጸመችው መጠነሰፊ የአየር እና የምድር ጥቃት ወደ ፍርስራሽነት ተቀይረዋል።
ሀማስ ጥቅምት ሰባት በፈጸመው ጥቃት ያገታቸውን እንዲለቅ እና እስራኤል ተኩስ ለማቆም እንድትስማማ ኳታር፣ ግብጹ እና አሜሪካ ጥረት እያደረጉ ይገኛሉ።