ድንገት የሜሲን ስም የጠሩት እናት እንዴት ራሳቸውን ከሀማስ ታደጉ?
ባለፈው ጥቅምት ወር የሀማስ ታጣቂዎች በአርጀንቲና የተወለዱት ኩኒዮ በሚኖሩበት ኪቡዝ ኒር ኦዝ ጨምሮ በጋዛ ድንበር ባሉ ቦታዎች ላይ ግድያ ፈጽመዋል
የ90 አመቷ እሸር ኩኒዮ ቤታቸውን ለወረሩት ሁለት ጭምብል ላጠለቁ የፍልስጤም ታጣቂዎች "ከሜሲ ሀገር ነው የመጣሁት" በማለታቸው ከጥቃት ድነዋል
ድንገት የሜሲን ስም የጠሩት እናት እንዴት ራሳቸውን ከሀማስ ታደጉ?
"እኔ የመጣሁት ከሜሲ ሀገር ነው" ሲሉ ነበር የ90 አመቷ እሸር ኩኒዮ ከደቂቃዎች በፊት በደቡብ እሰራኤል የሚገኘውን ቤታቸውን ለወረሩት ሁለት ጭምብል ላጠለቁ የፍልስጤም ታጣቂዎች ተናገሩት።
ባለፈው ጥቅምት ወር የሀማስ ታጣቂዎች በአርጀንቲና የተወለዱት ኩኒዮ በሚኖሩበት ኪቡዝ ኒር ኦዝ ጨምሮ በጋዛ ድንበር ባሉ ቦታዎች ላይ ግድያ ፈጽመዋል።
ኩኒዮ ያጋጠማቸውን አስፈሪ ክስተት የተናገሩት ሀማስ በላቲኖ ማህበረሰብ ላይ ያደረሰውን ጥቃት ትኩረት አድርጎ ለተሰራው "ቮሰስ ዴል ሰቨን ዲ ኦክቶበር- ላቲኖ ስቶሪስ ኦፍ ሰርቫይቫል" ለተሰኘው አዲስ ዘጋቢ ፊልም ነው።
ታጣቂዎቹ እኝህን እናት ሌሎች የቤተሰቦቻቸው አባላት የት እንዳሉ ሲጠይቋቸው ነበር።
"እኔን አታውራኝ፣ 'ምክንያቱም ቋንቋችሁን አልችልም' አልኩት ለታጣቂው። እናንተ አረብኛ ነው የምታወራው እኔ ደግሞ የተሰባበረ ኸርቢው ነው' የሚል መልስ ሰጠሁት። 'እኔ በአርጀንቲና ስፓኒሽ ነው የምናገረው' ብየ ነገርኩት ሲሉ ያስታውሳሉ።እሱ ደግሞ አርጀንቲና ምንድነው ብሎ ጠየቀኝ?'" ይላሉ ኩኒዮ።
ይህን ጊዜ ነበር ኩኒዮ በምልክት እና በተሰባበረ ኸርቢው ከታጣቂዎቹ ጋር እያወሩ እያለ ሜሲ የሚል ሰም የመጣላቸው።
"'እግር ኳስ ታያለህ' አልኩት? አዎ፤ አዎ እግር ኳስ እወዳለሁ' አለ። 'እኔ የመጣሁት ከሜሲ ሀገር ነው አልኩት። 'ሜሲ! ሜሲን አወደዋለሁ' አለኝ" ይላሉ ኩኒዮ።
ከእዚያ በኋላ አንደኛው ታጣቂ ክላሹን ኩኒዮን አሳቅፍ ጎንበስ ሲል ሌላኛው ፎቶ ማንሳቱን ተናግረዋል።
"እጁን እንዲህ አረገ ይላሉ" ኩኒዮ ሁለት ጣታቸውን ከፍ በማድረግ። "ፎቶ ካነሱ በኋላ ጥለው ሄዱ።"
ኩኒዮ አኬ-47 ክለሽ መሳሪያ ታቅፈው የፍለሴጤም አርማ ያለው ዩኒፎርም ከለበሰ እና ጭምብል ካጠለቀ ታጣቂ ጋር የተነሱት ፎቶ በማህበራዊ ሚዲያ በከፍተኛ መጠን ሲዘዋወር ነበር።
ነገርግን በኒር ኦዝ ሌላ ክፍል ያሉ የኩኒዮ ቤሰቦች ከእገታ አላመለጡም።
የልጅ ልጆቻቸው ዴቪድ እና አሪየል አሁንም በጋዛ ታገቱ። ከሚስቱ እና ከሁለት ልጆቹ ጋር የታገተው ዴቪድ ባለፈው ህዳር ወር በተደረገው ጦርነት ጋብ የማድረግ ስምምነት በፍልስጤም እስረኞች ለውጥ ተለቋል።
ኩኒዮ አሁን ላይ የልጅ ልጃቸውን መለቀቅ እየጠበቁ ነው።
የሀማስ ጥቃት እስካሁን አምስት ወራት ያስቆጠረው ጦርነት እንዲቀሰቀስ ምክንያት ሆኗል።
እሰራኤል ሀማስን ከምድረ ገጽ ለማጥፋት በጋዛ ላይ የከፈተችው መጠነሰፋ ጥቃት 2.3 ሚሊዮን የሚኖሩባትን ጋዛን ለከፍተኛ ሰብአዊ ቀውስ ዳርጓታል።