የፍልስጤም ጤና ባለስልጣናት እንደገለጹት በእስራኤል የአየር ድብደባ በጋዛ እስካሁን የሞቱ ሰዎች ቁጥር 10ሺ ደርሷል
ተመድ ዋና ጸኃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ "ጋዛ የህጻናት መቃብር እየሆነች ነው" ብለዋል።
የዋና ጸኃፊው ንግግር በጋዛ የሰብአዊ ተኩስ አቁም ያስፈልጋል የሚለውን ጥሪ የሚያጎላ ነው።
የፍልስጤም ጤና ባለስልጣናት እንደገለጹት በእስራኤል የአየር ድብደባ በጋዛ እስካሁን የሞቱ ሰዎች ቁጥር 10ሺ ደርሷል ።
በአሁኑ ወቅት በጋዛ ውስጥ ውጊያ እያካሄዱ ያሉት እስራኤል እና ሀማስ ተኩስ እንዲያቆሙ የቀረበላቸውን ጥሪ አልተቀበሉትም።
እስራኤል ተኩስ ለማቆም መጀመሪያ ሀማስ በጥቅምት ወር ጥቃት በመክፈት አፎኖ የወሰዳቸውን ይመልስ የሚል ቅድመ ሁኔታ ስታስቀምጥ፣ ሀማስ ደግሞ ጋዛ በጥቃት ውስጥ እያለች ታጋቾችን መመለስ የማይታሰብ ነው ብሏል።
ጉተሬዝ እንተደናገሩት "የእስራኤል ጦር በጋዛ ውስጥ በእግረኛ በሚያደርገው ጥቃት እና በቀጠለው ድብደባ ሰላማዊ ሰዎች፣ሆስፒታሎች፣ የስደተኛ ካምፖች፣ ቤተክርስቲያናት፣ መስጂዶች የተመድ ተቋማት እየተመቱ ናቸው። ማንም ደህንነቱ የተጠበቀ አይደለም።"
ዋና ጸኃፊው ሀማስ እና ሌሎች ታጣቂዎች ንጹሃንን እንደሰብአዊ ጋሻ በመጠቀም ሚሳይሎችን በዘፈቀደ ወደ እስራኤል እያስወነጨፉ ይገኛሉ ብለዋል።
ታጋቾቹ ያለቅድመ ሁኔታ እንዲለቀቁ ጉተሬዝ ጠይቀዋል።
ሀማስ በንጹሃን ዜጎች እና ሆስፒታል ውስጥ መደበቁን የምትገልጸው እስራኤል በጋዛ ውስጥ በእግረኛ ጦር ይዞታዋን ማስፋት ከጀመረች ወዲህ 31 ወታደሮች እንደተገደሉባት ገልጻለች።
ሀመስ በበኩሉ ሀማስ ሆስፒታል ውስጥ ተደብቋል የሚለው ክስ ተመድ ማረጋገጥ የሚችለው "የተሳሳተ ትርክት" ነው የሚል መልስ ሰጥቷል።
የአረብ ሀገራት በጋዛ ተኩስ እንዲቆም ቢጠይቁም፣ እስራኤል እና አጋሯ አሜሪካ ግን እንዲቆም አይፈልጉም።
አሜሪካ ተኩስ አቁም ማለት ሀማስ ተመልሶ እንዲደራጅ እና ጥቃት እንዲሰነዝር መፍቀድ ነው ብላለች።