ኔታንያሁ በጋዛ ጦርነት ኑክሌር የመጠቀም ሀሳብ ባቀረቡት ሚኒስትር ላይ እርምጃ ወሰዱ
ስለኑክሌር አማራጭነት ኢልያህ ለሬዲዮ በሰጡት ቃለ ምልልስ "አንዱ መንገድ" ነው ሲሉ መልሰዋል
የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁ በጋዛ ጦርነት ኑክሌር የመጠቀም ሀሳብ ያቀረቡትን ሚኒስትር ከኃላፊነት አግደዋል
ኔታንያሁ በጋዛ ጦርነት ኑክሌር የመጠቀም ሀሳብ ባቀረቡት ሚኒስትር ላይ እርምጃ ወሰዱ።
የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁ በጋዛ ጦርነት ኑክሌር የመጠቀም ሀሳብ ያቀረቡትን ሚኒስትር ከኃላፊነት አግደዋል።
ከሀማስ ጋር እየተካሄደ ያለው ጦርነት በፍልስጤማውያን ንጹሃን ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰ ባለበት ወቅት እስራኤል በጋዛ ጦርነት ኑክሌር እንድትጠቀም ሀሳብ ያቀረቡት ሚኒስትር የእግድ እርምጃ እንደተወሰደባቸው ሮይተርስ ዘግቧል።
ኔታንያሁ በጥምር መንግስቱ ውስጥ የቀኝ ዘመሙ ፖርቲ አባል የሆኑት የሄሪቴጅ ሚኒስትሩ አሚሃይ ኢሊያሁ ምርመራ እስካጣራ ከካቢኔ ስብሰባ መታገዳቸውን ተናግረዋል።
ስለኑክሌር አማራጭነት ኢልያህ ለሬዲዮ በሰጡት ቃለ ምልልስ "አንዱ መንገድ" ነው ሲሉ መልሰዋል።
የሚኒስትሩ ንግግር በአረቡ አለም ከፍተኛ ውግዘት አስከትሏል።
ኢሊያህም ይሁኑ ፖርታያቸው በጋዛ እየተካሄደ ያለውን ጦርነት በዋናነት በሚመራው ስብስብ ውስጥ አልተካተቱም። ሁለቱም እስራኤል የኑክሌር አቅም እንዳት የሚያቁነት ነገር ስለመኖሩ ያሉት ነገር የለም።
"የኢሊያህ ንግግር በእውነታ ላይ የተመሰረተ አይደለም። እስራኤል እና ጦሯ ንጹሃን እንዳይጎዱ አለምአቀፍ ህግን መሰረት በማድረግ ነው ጦርነቱን የምታካሂደዎ። ድል እስከምናደርግ እንዲሁ እንቀጥላለን" ብለዋል ኔታንያሁ።
እስራኤል ከሀማስ ጋር በምታደርገው ጦርነት ከኔታንያሁ ጋር የቆሙት ተቃዋሚው ቤኒ ጋንዝ የኢሊያህ አስተያየት አጥፊ ነው ሲሉ ተችተዋል።
እስሳኤል በጥቅምት ወር ድንበር ጥሶ 1400 ገድሎ እና 240 ዜጎቿን ያገተባትን ሀማስን ከምድረ ገጹ ለማጥፋት አልማ እያካሄደች ያለውን ጦርነት አሁንም ቀጥላለች
የታጋቾች ቤተሰቦች በጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁ መንግስት ላይ ቤተሰቦቻቸውን ለማስለቀቅ በቂ ጥረት አላደረገም በሚል ከፍተኛ ተቃውሞ እያሰሙ ነው።
ሀማስ በትናንትናው እለት ከታጋቾቹ ውስጥ 60 የሚሆኑት በእስራአል የአየር ጥቃት ምክንያት የት እንዳሉ እንደማያወቅ ገልጿል።
በጋዛ ተኩስ እንዲቆም ጥሪ ቢደረግም እስራኤል አይሆንም ብላለች።