የእስራኤል ሃማስ ጦርነት ምን አዳዲስ ክስተቶችን አስተናግዷል? እስካሁን የምናውቀው
እስራኤል አዳሩን በጋዛ በፈጸመችው የአየር ድብደባ ቢያንስ 19 ሰዎች ሞተዋል
በዌስት ባንክ በተፈጸመ ጥቃት ቢያንስ 2 እስራኤላውያን ሰፋሪዎች ተጎድተዋል
ሃማስ በእስራኤል ላይ ድንገተኛ እና ያለተጠበቀ ጥቃት መሰንዘሩን ተከትሎ የተቀሰቀሰው ጦርነት አሁንም እንደቀጠለ ነው።
እስራኤል ጦር አዳሩን በጋዛ ላይ የማያባራ የአየር ድብደባ ሲያደረግ ያደረ ሲሆን፤ በአየር ድብደባውም ቢሃንስ 24 ፍሊስጤማውያን ተገድለዋል።
በዚህም 19ፍሊስቴማውያን በጀባሊያ መጠለያ ካምፕ አካባቢ በሚገኝ ሆስፒታል፣ 4 ደግሞ በካሃን ዩኒስ በተባለ ስፍራ ነው።
የእስራኤል ጦር ሀየብሮን አካባቢ ባደረገው ወረራ ደግሞ 1 ሰው ገድሏል።
የእስራኤል ቡልዶዘሮች በርካታ የሃማስ ዋሻዎችን ማፈራረሰቸው የተገለፀ ሲሆብ፣ በቤኒን ዋናውን አስፋልት መንገድ አፈራርሷል።
ሃማስ በእስራኤል ላይ የሚፈጽመውን ጥቃት አጠናክሮ ቀጥሏል፣ በዌስት ባንክ ነብሉስ አካባቢ ሁለት እስራኤላውያን ሰፋሪዎች ከፉኛ ተጎድተዋል።
የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንሃሁ፣ እስራኤል የተኩስ አቁም ልታደርግን ነው ማለቱን አስተባብለው፣ ታጋቾች እስኪለቀቁ ድረስ ድብደባው ይቀጥላል ብለዋል።
የሊባኖሱ ሄዝቦላህ እስራኤል በጋዛ የምታካሂደው የአየር ድብደባ ካልቆመ ቀጠናዊ ጦርነት ሊቀሰቀስ ይችላል ሲል አስጠንቅቋል።
ጦርነቱ ያስከተለው ሞትና ሰብዓዊ ቀውስ
እስራኤል በጋዛ እያካሄገችው ያልተቋረጠ የአየር ድብደባ ተከትሎ በጋዛ የሞቱ ፍሊስጤማውያን ቁጥር ከ10 ሺህ 500 ያለፈ ሲሆን ከ25 ሺህ በላይ ደግሞ ቆስለዋል።
በዌስት ባንክ ደግመለ 163 ፍሊስጤማውያን የሞቱ ሲሆን፣ ከ2 ሺህ በላይ ደግሞ ቆስለዋል።
በእስራኤል የሃማስጥን ጥቃት ተከትሊ የሞቱ ሰዎች ቁጥር 1405 ላይ የቆመ ሲሆን፣ 5 ሺህ 600 ገደማ ሰዎች ቆስለዋል።