ሩሲያ የእስራኤል የኑክሌር አስተያየት "ብዙ ጥያቄዎችን" የሚያስነሳ ነው አለች
ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁ የቀኝ ዘመም ፖርቲ አባል የሆኑትን የሄርቴጅ ሚኒስትር አምሃይ ኢሊያህን ባቀረቡት ኃሳብ ምክንያት ከኃላፊነት አግደዋቸዋል
" ኑክሌር መኖሩን የሚያረጋግጥ ይፋዊ መግለጫ እየሰማን ነውን"ሲሉ ዛካሮቫ ይጠይቃሉ
ሩሲያ የእስራኤል የኑክሌር አስተያየት "ብዙ ጥያቄዎችን" የሚያስነሳ ነው አለች።
የሩሲያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በዛሬው እለት እንደገለጸው በጋዛ ጦርነት ኑክሌር የመጠቀም ሀሳብ ያቀረበት ሚኒስትር ጉዳይ በርካታ ጥያቄዎችን አስነስቷል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁ የቀኝ ዘመም ፖርቲ አባል የሆኑትን የሄርቴጅ ሚኒስትር አምሃይ ኢሊያህን ባቀረቡት ኃሳብ ምክንያት ከኃላፊነት አግደዋቸዋል።
ኢሊያህ በአንድ የሬድዮ ቃለ ምልልስ ላይ እንደተናገሩት ኑክሌር መጠቀም "አንዱ መንገድ ነው" የሚል መልስ ሰጥተዋል።
የሩሲያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ማሪያ ዛካሮቫ "ይህ ብዙ ጥያቄዎችን ያስነሳል" ማለታቸውን የሩሲያው ሪያ ኤጀንሲ ዘግቧል።
ዛካሮቫ ዋናው ጉዳይ እስራኤል ኑክሌር መታጠቋን ያመነች ይመስላል ብለዋል።
የአሜሪካ ሳይንቲስቶች ፌደሬሽን እስራኤል 90 የኑክሌር ተተኳሽ እንዳላት ቢገልጽም፣ እስራኤል ግን በአደባባይ ኑክሌር እንዳላት አልገለጸችም።
"የመጀመሪያው ጥያቄ- ኑክሌር መኖሩን የሚያረጋግጥ ይፋዊ መግለጫ እየሰማን ነውን"ሲሉ ዛካሮቫ ይጠይቃሉ።
ይህ ከሆነ የአለምአቀፍ አቶሚክ ኢነርጂ እና አለምአቀፍ የኑክሌር መርማሪዎች የት አሉ እያሉ ሌላ ጥያቄ ይጠይቃሉ።
የኢሊያህ አስተያየት በተለይም ከአረቡ አለም አለምአቀፍ ውግዘትን አስሰትሏል።