በእስራኤል ጦር ውሾች በአሰቃቂ ሁኔታ ተነካክሶ ህይወቱ ያለፈው የአዕምሮ ህመምተኛ ፍልስጤማዊ
የ24 ዓመቱ ሙሃመድ ባር በመኖሪያ ቤቱ በእስራኤል ጦር ውሾች በደረሰበት ጉዳት ህይወቱ አልፏል
የእስራኤል ጦር የኦቲዝም ተጠቂው ፍልስጤማዊ በቤተሰቦቹ ፊት በውሾች እንዲነከስ ካደረገ በኋላ በኋላ ህክምና እና ቤተሰቦቹ እንዳያገኙት አድርጓል ተብሏል
በእስራኤል ጦር ውሾች በአሰቃቂ ሁኔታ ተነካክሶ ህይወቱ ያለፈው የአዕምሮ ህመምተኛ ፍልስጤማዊ
መሀመድ ባር የተሰኘው የ24 ዓመት ወጣት ፍልስጤማዊ ሲሆን በጋዛ ሼጃያ በተሰኘችው መንደር ውስጥ ከቤተሰቦቹ ጋር ይኖር ነበር፡፡
እነዚህ ፍለስጤማዊያን የእስራኤል ጦር ወደ ጋዛ መግባቱን ካሳወቀበት ጊዜ ጀምሮ ነፍሳቸውን ለማትረፍ ከ15 ጊዜ በላይ ቤታቸውን እየለቀቁ ሲሰደዱ ቆይተዋል፡፡
ከሶት ሳምንት በፊት የእስራኤል እግረኛ ጦር የሐማስ ታጣቂዎን ለመደምሰስ በሚል ወደ በድንገት ሼጃያ መንደር ሲገባ እንደ ከዚህ ቀደሙ መሸሽ አልቻሉም፡፡
በተለይም የአዕምሮ ህመምተኛ የሆነው መሃመድን ይዞ መሰደድ ደግሞ ከባድ በመሆኑ በቀላሉ ከቤታቸው መውጣ እንዳልቻሉ እናቱ ናቢላ ለቢቢሲ ተናግራለች፡፡
በመጨረሻም የእስራኤል ወታደሮች እና ውሾቻቸው ወደ ተደበቅንበት ቤት መጡ እና አገኙን የምትለው እናቱ ናቢያ ከቤት እንድንወጣ አስገደዱን ብላላች፡፡
ነገር ግን ውሾቹ ድንገት መሃመድን መንከስ ጀምሩ፣ ልናስቆማቸው ስንሞክር ወታደሮቹ ከለከሉን፣ እነሱም እንዲያስጥሉት ብንነግራቸውም እንቢ አሉን ስትልም ተናግራለች፡፡
መሀመድ የዐዕምሮ ህመምተኛ ነው ራሱን መከላከልም ሆነ መመገብ አይችልም እባካችሁ እንርዳው ብንልም ከመፍቀድ ይልቅ አካባቢውን ጥለው እንዲሄዱ እንዳስገደዷቸው አክላላች፡፡
በውሾች ንክሻ ምክንያት ፊቱ እና ደረቱ በደም ተሸፍኖ ሳየው አልቻልኩም የምትለው እናቱ የእስራኤል ጦር ሐኪሞች ጠርተን እናሳክመዋለን እናንተ ከዚህ ራቁ ብለውን ከአካባቢው እንዲሁዴ መደረጋቸውንም ተናግራለች፡፡
ከአንድ ሳምንት በኋላ ወደ ቤት በድብቅ ስንመለስ ግን መሀመድ ደም ፈሶት ህይወቱ በአሰቃቂ ሁኔታ አልፎ አገኘነው ያለችው እናቱ ናቢላ በልጃቸው ላይ አሰቃቂ ግድያ እንደተፈጸመበት፣ የእስራኤል ጦር ውሾች ልጇን እንዴት ሲነክሱት እንደነበር እድሜ ልኳን እንደማትረሳውም ገልጻለች፡፡
እስራኤል የወታደራዊ አገልግሎት ጊዜ እንዲራዘም ወሰነች
የእስራኤል ጦር በበኩሉ ጉዳዩን እየመረመረ መሆኑን ለቢቢሲ ምላሽ ሰጥቷል፡፡
ከ10 ወራት በፊት ለፍልስጤም ነጻነት እታገላለሁ የሚለው ሐማስ በእስራኤል ላይ ያልታሰበ ጥቃት መሰንዘሩን ተከትሎ ነበር በጋዛ እና አካባቢው ጦርነት የተቀሰቀሰው፡፡
በዚህ ጦርነት ምክንያት ከ38 ሺህ በላይ ፍልስጤማዊያን ዜጎች በእስራኤል ጦር ሲገደሉ ከሟቾች ውስጥ አብዛኞቹ ህጻናት እና ሴቶች እንደሆኑ የተመድ ሪፖርት ያስረዳል፡፡ እንዲሁም ከ1 ሺህ 200 በላይ እስራኤላዊን ደግሞ በሐማስ ታጣቂዎች መገደላቸው ተገልጿል፡፡
ይህ በዚህ እንዳለ ግን በርካታ ሀገራ እና የሰብዓዊ መብት ተቋማት እስራኤል የጦር ወንጀል መፈጸሟን የሀገሪቱ ከፍተኛ መሪዎችም በዚሁ የጦር ወንጀል ሊጠየቁ ገባል ሲሉ በመወትወት ላይ ናቸው፡፡