የየመን ሀውቲ ታጣቂዎች በኤደን ባህረ ሰላጤ እና በእስራኤል ኢላት ወደብ ጥቃት መክፈታቸውን ገለጹ
ቃል አቀባዩ እንደገለጸው የአሁኑ የሀውቲ ጥቃት እስራኤል በካን ዮኒስ የፈጸመችውን እና ቢያንስ 90 ሰዎች የገደሉበትን ጥቃት ለመበቀል ነው።
የሀውቲ ታጣቂዎች ከባለፈው ህዳር ጀምሮ በቀይ ባህር እና በኤደን ባህረ ሰላጤ በሚንቀሳቀሱ የንግድ መርከቦች ላይ ጥቃት እያደረሱ ነው
የየመን ሀውቲ ታጣቂዎች በኤደን ባህረ ሰላጤ እና በእስራኤል ኢላት ወደብ ጥቃት መክፈታቸውን ገለጹ።
የየመን ሀውቲ ታጣቂዎች በኤደን ባህረ ሰላጤ እና በደቡብ እስራኤል ጫፍ በምትገኘው ኢላት ወደብ ላይ ጥቃት መክፈታቸውን በትናንትናው እለት አስታውቀዋል።
የሀውቲ ወታደራዊ ቃል አቀባይ ያህያ ሰርኤ፣ ቡድኑ በኢላት ወደብ ያሉ ወታደራዊ ኢላማዎችን ከማጥቃት በተጨማሪ በኤደን ባህረ ሰላጤ የእስራኤሏን ኤምኤስሲ ዩኤንአይኤፍአይሲ መርከብን በባለስቲክ ሚሳይሎች እና ድሮኗች ማጥቃቱን ገልጿል።
ቃል አቀባዩ እንደገለጸው የአሁኑ የሀውቲ ጥቃት እስራኤል በካን ዮኒስ የፈጸመችውን እና ቢያንስ 90 ሰዎች የገደሉበትን ጥቃት ለመበቀል ነው።
የአሜሪካ ማዕከላዊ እዝ ባወጣው ሌላ መግለጫ በኢራን የሚደገፉትን የሀውቲ ታጣቂዎች ሁለት ድሮኖችን ቀይ ባህር ላይ እና ሌላ አንድ ድሮን በሀውቲዎች ይዞታ ውስጥ ማውደሙን አስታውቋል።
"እነዚህ ሲስተሞች (ድሮኖች) ለአሜሪካ እና በቀጣናው ለተሰማራው ጥምር ኃይል አደጋ ደቅነዋል"ሲል ማዕከላዊ እዙ አክሎ ገልጿል። የሀውቲ ታጣቂዎች ከባለፈው ህዳር ጀምሮ በቀይ ባህር እና በኤደን ባህረ ሰላጤ በሚንቀሳቀሱ የንግድ መርከቦች ላይ ጥቃት እያደረሱ ነው። ቡድኑ ይህን ጥቃት የሚፈጽመው በጋዛ ጦርነት ለተጎዱ ፍልስጤማውያን አጋርነት ለማሳየት መሆኑን አሳውቋል።
ቡድኑ በፈጸማቸው በርካታ ጥቃቶች ሁለት መርከቦች እንዲሰጥሙ ማድረጉ እና ሌላ አንድ በቁጥጥር ስር ማድረጉ ይታወሳል።