የፍሊስጤም ስታተስቲክስ ቢሮ ከጦርቱ ወዲህ የጋዛ ህዝብ ቁጥር 160 ሺህ ገደማ ቅናሽ አሳይቷል ብሏል
የጋዛ ህዝብ ቁጥር በ6 በመቶ መቀነሱን የፍሊስጤም ማዕከላዊ ስታተስቲክስ ቢሮ ከሰሞኑ ባጋራው መረጃ አመላክቷል።
ቢሮው ባወጣው መረጃው የጋዛ የህዝብ ቁጥር በከፍተኛ ደረጃ የቀነሰው በሃማስ እና እስራኤል መካከል የተቀሰቀሰውን ጦርት ተከትሎ ነው።
በዚህም መሰረት የጋዛ ህዝብ ቁጥር በአጠቃላይ ከነበረበት በ160 ሺህ ገደማ ቀንሷል ያለው ቢሮው፤ ከእነዚህም ውስጥ 55 ሺህ ያከሉ መሞታቸው እና 100 ሺህ ሰዎች ደግሞ ጋዛን ለቀው መውጣታቸውን አስታውቋል።
ይህንን ተከትሎም የፍልስጤም ማዕከላዊ የስታትስቲክስ ቢሮ (ፒሲቢኤስ) እንደገመተው ከሆነ እስራኤል ጋዛ ላይ ጦርነት ከጀመረችበት ጊዜ አንስቶ የጋዛ ህዝብ በ6 በመቶ ገደማ ቅናሽ አሳይቷል።
የጋዛ የጤና ሚኒስቴር ባጋራው መረጃ ከሆነ በእስራኤል የአየር እና የምድር ላይ ጥቃቶች በጋዛ ውስጥ የሞቱ ፍሊስጤማውያን ቁጥር 45 ሺህ ነው ብሏል።
የፍልስጤም ማዕከላዊ የስታትስቲክስ ቢሮ (ፒሲቢኤስ) በበኩሉ እስራኤል በጋዛ ላይ ወረራ ከፈጸመችበት እለት አንስቶ የሞቱ ፍስጤማውያን ቁጥር 55 ሺህ መሆኑን እና 11 ሺህ ሰዎች መጥፋታቸውን እንዲሁም 100 ሺህ ሰዎች ጋዛን ለቀው መሰደዳቸውን አስታውቋል
እንደ የፍልስጤም ማዕከላዊ የስታትስቲክስ ቢሮ መረጃ ከሆነ አሁን ላይ የጋዛ የህዝ ቁጥር በ160 ሺህ ቀንሶ 2.1 ሚሊየን መሆኑን ያመለክል።
የእስራኤል የውጭ ጉዳይ ሚኒስር በበኩሉ የፍልስጤም ማዕከላዊ የስታትስቲክስ ቢሮ (ፒሲቢኤስ) ያጋራው መረጃ ከእውነት የራቀ የፈጠራ መረጃ ነው በማለት አጣጥሎታል።