ጋዛን መልሶ ለመገንባት እስከ 50 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር እንደሚያስፈልግ ተመድ አስታወቀ
ተመድ በጋዛ ከሚገኙ ቤቶች ውስጥ 70 በመቶው መውደማቸው ገልጿል
በጋዛ ውስጥ ላለፉት 40 ዓመታት ሁሉም ልማቶችና ኢንቨስትመንቶች በጦርነቱ ወድመዋል
በጋዛ ጦርነት ያወደመውን መልሶ ለመገንባት 50 ቢሊየን ዶላር እንደሚያስፈልግ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታወቀ።
የተመድ የልማት ፕሮግራም ትናንት በሰጠው መግለጫ፤ በጋዛ የደረሰው ውድመት ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወዲህ በየትኛውም ቦታ ታይቶ የማይታወቅ ነው ብሏል።
ጋዛን ከጦርነት በኋላ መልሶ ለመገንባትመ እስከ 50 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር ድረስ ሊያስፈፈልግ እንደሚችልም ነው የተመድ የልማት ፕሮግራም የስራ ኃላፊ የተናሩት።
በተባበሩት መግስታት የልማት ፕሮግራም የአረብ ሀገራት ቀጠናዊ ቢሮ ኃላፊ አብደላህ አል-ዳርዳሪ፤ “ከፈረንጆቹ 1945 ወዲህ በዓለም ላይ እንዲህ አይነት ውድመት አይተን አናውቅም” ብለዋል።
በጋዛ ከሚገኙ ቤቶች ውስጥ 70 በመቶው ወድመዋል ያሉት ኃላፊው፤ 37 ሚሊየን ቶን ፍርስራሽ ማነሳት እንደሚጠበቅም አስታውቀዋል።
በፈረንጆቹ በ2014 ከተካሄደው የሃማስ እስራኤል ጦርነት ወቅት ከተነሳው 2.4 ሚሊየን ፍርሰራሽ ጋር ሲነጻርም ቁጥሩ ከፍተኛ መሆኑን ኃላፊው ተናግረዋል።
በአጠቃላይ ባለፉት ስድስት ወራት በጋዛ የተካሄደው ጦርነት የጋዛን ልማት በ40 ዓመታት ወደኋላ የመለሰ መሆኑን የተመድ የልማት ፕሮግራም አስታውቋል።
ባለፉት 40 ዓመታት በሰው ልጆች ልማት ላይ የተሰሩ ሁሉም ኢንቨስትመንቶች ሙሉ በሙሉ መውደማቸውንም ነው ኃላፊው የተናገሩት።
ከጦርነት በኋላ ጋዛን መልሶ ለመገንባትም ከ40 እስከ 50 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር አንደሚያስፈልግም አብደላህ አል-ዳርዳሪ በመግለጫቸው ተናግረዋል።
የእስራኤል ጦር ከጥቅም ት 7 ጀምሮ በጋዛ ያለማቋረጥ የአየር ድብደባ እያደረገ ሲሆን፤ በእስራኤል ድብደባም እስካን ከ34 ሺህ 500 በላይ ፍሊስጤማውያን ህይወታቸውን አጥተዋል።