ፖለቲካ
የእስራኤል 70 ሺህ ቶን ቦምብ በጋዛ ያደረሰው ውድመት
የአለም ባንክ በህዝብ መገልገያ ተቋማት ላይ የደረሰው ውድመት 18 ነጥብ 5 ቢሊየን ዶላር እንደሚደርስ ገምቷል
ጋዛን ማፈራረሱን የቀጠለው ጦርነት ከ1 ሚሊየን በላይ ሰዎችን ቤት አልባ አድርጓል ተብሏል
ስድስት ወር ያስቆጠረው የእስራኤል የጋዛ ጦርነት የሰርጡን 62 በመቶ ቤቶች አፈራርሷል።
ከ1 ሚሊየን በላይ ፍልስጤማውያን ጦርነቱ ቆሞ ወደቀያቸው ቢመለሱ የሚያርፉበት ጎጆ የላቸውም ተብሏል።
የአለም ባንክ በህዝብ መገልገያ ተቋማት ላይ የደረሰው ውድመት 18 ነጥብ 5 ቢሊየን ዶላር እንደሚደርስ ገምቷል።
እስራኤል በጋዛ ሰርጥ 70 ሺህ ቶን ቦምብ ማዝነቧን የሚገልጸው የአናዶሉ ዘገባ የደረሰው ውድመት ከዚህም ሊልቅ እንደሚችል ጠቁሟል።
ዩኒሴፍ በጋዛ ከአስር ትምህርት ቤቶች ስምንቱ ወድመዋል ወይም ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸዋል የሚል መግለጫን አውጥቷል።
እስራኤል የሃማስ ታጣቂዎች ይገኙባቸዋል በሚል በሆስፒታሎች ላይ በፈጸመችው ጥቃትም ከ36 የጋዛ ሆስፒታሎች 32ቱ ጉዳት ደርሶባቸዋል።
የአለም ጤና ድርጅት በቅርቡ ባወጣው መረጃ በጋዛ በከፊል አቅማቸው እየሰሩ የሚገኙት 10 ሆስፒታሎች ብቻ ናቸው ማለቱ የሚታወስ ነው።
በመስጂዶች እና ቤተክርስቲያኖች ላይ የተፈጸመው ድብደባም ከባድ ጉዳት አድርሷል።
እስራኤል ባለፉት ስድስት ወራት በጋዛ በፈጸመችው ድብደባ የደረሰውን ውድመት በቀጣዩ ምስል በዝርዝር ይመልከቱ፦