የጋዛን ፍርስራሽ ለማጽዳት 14 አመታትን ሊፈጅ እንደሚችል ተመድ ገለጸ
ባለሙያው እንደገለጹት ጥቅም ላይ ከሚሉት ተተኳሾች ውስጥ 10 በመቶ የሚሆኑት ከተተኮሱ በኋላ አይፈነዱም
እስራኤል ሀማስን ለማጥፋት በወሰደችው ወታደራዊ ዘመቻ 2.3 ሚሊዮን ህዝብ የሚኖርባትን ጠረፋማዋን ግዛት ወደ ፍርስራሽነት ቀይራታለች
የጋዛን ፍርስራሽ ለማጽዳት 14 አመታትን ሊፈጅ እንደሚችል ተመድ ገለጸ።
እስራኤል በጋዛ ባደረሰችው አውዳሚ ጦርነት ያልፈነዱ መሳሪያዎችን ጨምሮ ፍርስራሾችን ለማጽዳት 14 አመታት ገደማ ሊፈጅ እንደሚችል የተመድ ባለስልጣን በትናንትናው እለት ተናግረዋል።
እስራኤል የጋዛ ሰርጥን የሚያስተዳድረውን ሀማስን ለማጥፋት በወሰደችው ወታደራዊ ዘመቻ 2.3 ሚሊዮን ህዝብ የሚኖርባትን ጠረፋማዋን ግዛት ወደ ፍርስራሽነት ቀይራታለች፤ አብዛኞቹ ነዋሪዎች ቤት አልባ እና ተፈናቃይ ሆነዋል።
በተመድ ማይን አክሽን ሰርቪስ (ዩኒኤምኤኤስ) ከፍተኛ ባለሙያ የሆኑት ፒህር ሎሀመር በጀኔቫ በሰጡት ጋዜጤዊ መግለጫ እንደተናገሩት ጦርነቱ በግምት 37 ሚሊዮን ቶን ፍርስራሽ እንዲከማች አድርጓል።
በጋዛ ምን ያህል ያልፈነዱ የጦር መሳሪያዎች መኖራቸውን መገመት እንደማይቻል የገለጹት ባለሙያው ከወደሙ ህንዳዎች ውስጥ ያለውን ቆሻሻ ጨምሮ ፍርስራሾችን ለማጽዳት 14 አመታት ሊፈጅ ይችላል ብለዋል።
ባለሙያው እንደገለጹት ጥቅም ላይ ከሚሉት ተተኳሾች ውስጥ 10 በመቶ የሚሆኑት ከተተኮሱ በኋላ አይፈነዱም።
ባለፈው ጥቅምት ወር ሀማሰ የእስራኤልን ድንበር በመጣስ 1200 ሰዎችን መግደሉን እና 240 የሚሆኑትን አግቶ መውሰዱን ተከትሎ የተቀሰቀሰው የእስራኤል እና ሀማስ ጦርነት እስከሁን እንደቀጠለ ነው።
እስራኤል በጋዛ እየወሰደች ባለው መጠነ ሰፊ የአየር እና የምድር ጥቃት የተገደሉ ፍልስጤማውያን ቁጥር ከ34ሺ ማለፉን የጋዛ ጤና ባለስልጣናት ገልጸዋል።
እስራኤል እና ሀማስ ለማድራደር የተደረገው ጥረትም አንዳቸው ሌላኛቸው ያቀረቡትን ቅድመ ሁኔታ ውድቅ እያደረጉ በመቀጠላቸው እስካሁን አልተሳካም።