ጋዛ ከምድረ ገጽ ልትጠፋ እንደምትችል የስነ ምድር ተመራማሪው ተናገሩ
እስራኤል በጋዛ እያካሄደች ያለው ጦርነት አሸባሪዎችን መዋጋት እንዳልሆነ ተመራማሪው ገልጸዋል
በህዝብ ተሞልታ የነበረችው ጋዛ ወደ እስራኤል ግዛት መጠቃለሏ አይቀሬ ይሆናልም ተብሏል
ጋዛ ከምድረ ገጽ ልትጠፋ እንደምትችል የስነ ምድር ተመራማሪው ተናገሩ።
ታዋቂው የስነ ምድር ተመራማሪው ፍራንክ ሁገርቢትዝ እንዳለው ጋዛ ከምድረ ገጽ ልትጠፋ እንደምትችል ገልጸዋል።
ሆላንዳዊ ተመራማሪ በቀድሞ ስሙ ትዊተር ወይም አሁን ላይ ኤክስ ተብሎ በሚጠራው የትስስር ገጻቸው ላይ እንዳሉት ጋዛ ስሟ ከምድር ላይ ሊጠፋ እንደሚችል ተናግረዋል።
እስራኤል በህዝብ ብዛት ተጨናንቃ በነበረችው ጋዛ ላይ የአየር እና ምድር ላይ ጥቃት መክፈቷ አካባቢዋን ከምድረገጽ የሚያጠፋ እንደሆነም ተመራማሪው ገልጸዋል።
"የምናውቃት ጋዛ አሁን ያለችበትን ሁኔታ ይዛ ልትቀጥል አትችልም፣ ወደ እስራኤል ግዛትነት መካተቷ እና ስሟም ሊቀየር ይችላል" ሲሉም ተመራማሪው አክለዋል።
እስራኤል ወደ ጋዛ ያመራችው አሸባሪዎችን ለመታገል እንዳልሆነ የሚናገሩት ተመራማሪው እስራኤል ከ1948 ጀምሮ ፍልስጤማዊያንን እያባረረች መሆኗንም ጠቅሰዋል።
ከእስራኤል ጦር ጋር እየተዋጋ ያለው ሀማስ የተኩስ አቁም ለማድረግ ፈቃደኛ መሆኑን ቢገልጽም እስራኤል ግን ጥቃቷን ቀጥላለች ተብሏል።
ግብጽ በበኩሏ እስራኤል ፍልስጤማዊያንን ወደ ሲናይ በረሀ በግድ የማዛወር እቅድ እንዳላት ደርሼበታለሁ ማለቱ ይታወሳል።
ሲናይ በረሀን የጎበኙት የግብጽ ጠቅላይ ሚንስትር ለሲናይ ሚሊዮን ግብጻዊያንን እንደሚያሰለፉም ለእስራኤል እቅድ ምላሽ ሰጥተዋል።