እስራኤል የደቡብ አፍሪካ አምባሳደሯን ጠራች
ደቡብ አፍሪካ በቅርቡ ያወጣችውን መግለጫ ተከትሎ እስራኤል በደቡብ አፍሪካ ያሉትን አምባሳደሯን ለምክክር መጥራቷን የእስራኤል ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገልጿል
እስራኤል በጋዛ እያካሄደች ያለውን ዘመቻ በጽኑ የምትቃወመው ደቡብ አፍሪካ በእስራኤል ያሉትን አምባሳደሯን መጥራቷ ይታወሳል
እስራኤል የደቡብ አፍሪካ አምባሳደሯን ለምክክር ጠርታለች።
ደቡብ አፍሪካ በቅርቡ ያወጣችውን መግለጫ ተከትሎ እስራኤል በደቡብ አፍሪካ ያሉትን አምባሳደሯን ለምክክር መጥራቷን የእስራኤል ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገልጿል።
የደቡብ አፍሪካው ገዥ ፖርቲ አፍሪካን ናሽናል ኮንግረስ(ኤኤንሲ) እንደገለጸው ባለፈው ሀሙስ በደቡብ አፍሪካ ያለው የእስራኤል ኢምባሲ እንዲዘጋ በፖርላማ የቀረበውን የውሳኔ ሀሳብ ይደግፋል።
እስራኤል በጋዛ እያካሄደች ያለውን ዘመቻ በጽኑ የምትቃወመው ደቡብ አፍሪካ በእስራኤል ያሉትን አምባሳደሯን መጥራቷ ይታወሳል።
ደቡብ አፍሪካ፣ በሀማስ ላይ የአጸፋ እርምጃ እየወሰች ባለችው እስራኤል ላይ ተቃውሞዋን የገለጸችው ንጹሃን እየተጎዱ ነው በሚል ምክንያት ነው።
የደቡብ አፍሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባለፈው ወር ባወጣው መግለጫ እስራኤል አለምአቀፍ ህጎችን በመጣስ በንጹሃን ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰች ነው ሲል ነበር ተቃውሞውን ያቀረበው።
ከደቡብ አፍሪካ በተጨማሪ በደርዘን የሚቆጠሩ ሀገራት የእስራኤልን ድርጊት በመቃወም አምባሳደሮቻቸውን መጥራታቸው ይታወሳል።
በጋዛ የተኩስ አቁም እንዲደረግ አለምአቀፍ ጫና ቢደረግም፣ እስራኤል እና አጋሯ አሜሪካ እስካሁን አልተቀበሉትም።