የሚሊኒየሙ ትውልድ ከቀድሞው ትውልድ የበለጠ ለካንሰር ተጋላጭ መሆኑን ጥናት አመለከተ
የሚሊኒየሙ ትውልድ ከቀድሞው ጋር ሲነጻጸር በ17 የካንሰር አይነት ተጋላጭ ነው ተብሏል
አመጋገብ እና የህይወት ዘይቤ መቀየር በካንሰር የሚጠቁ ዜጎች ቁጥር እንዲጨምር ምክንያት እንደሆነ በጥናቱ ለይ ተገልጿል
የሚሊኒየሙ ትውልድ ከቀድሞው ትውልድ የበለጠ ለካንሰር ተጋላጭ መሆኑን ጥናት አመለከተ፡፡
የሰዎች አኗኗር ዘይቤ በየጊዜው የሚቀያየር እና የሚለዋወጥ ሲሆን ይህም የጤና ሁኔታዎችን እንደሚቀይር ይታወቃል፡፡
ከፈረንጆቹ ዘመን አቆጣጠር 1981 እስከ 1996 ባሉት ዓመታት ውስጥ የተወለዱ ሰዎች በተለምዶ የሚሊኒየም ትውልድ በመባል ይታወቃል፡፡
በዚህ ስሌት መሰረት እድሜያቸው ከ28 እስከ 43 ዓመት የሆናቸው ዜጎች ከዚህ በፊት ከተወለዱት ጋር ሲነጻጸር የበለጠ ለካንሰር ህመሞች የመጋለጥ እድላቸው ከፍተኛ መሆኑን አንድ ጥናት አመለክቷል፡፡
ላንሴት የተሰኘው የህዝብ ጤና ጥናት ተቋም ይፋ እንዳደረገው ከሆነ የሚሊኒየም ትውልድ ከዚህ በፊት ታይተው ባልነበሩ 17 የካንሰር ህመም አይነቶች ተጋልጠዋል፡፡
ኢትዮጵያ H5170 በሚል ስያሜ ለጡት ካንሰር ታማሚዎች የሚሰጠው መድሃኒት ጥቅም ላይ እንዳይውል አሳሰበች
የአሜሪካ ካንሰር ማህበረሰብ ከካናዳው ካግላሪ ዩንቨርሲቲ ጋር ያስጠናው እና በላንሴት የምርምር ማዕከል አማካኝነት ይፋ የተደረገው ይህ ጥናት አሁን ላይ 34 አይነት የካንሰር ህመም አይነቶች 24 ሚሊዮን ሰዎን አጥቅተዋል ብሏል፡፡
በነዚህ ህመሞች ምክንያትም በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ዜጎች ህይወታቸውን አጥተዋል የተባለ ሲሆን የሚሊኒየም ትውልድ ከ1960ዎቹ ትውልድ ጋር ሲነጻጸሩ የበለጠ ተጋላጭ እንደሆኑ ተገልጿል፡፡
አሁን ላይ የሚሊኒየም ትውልድ የተባለውን የማህበረሰብ ክፍል እያጠቁ ካሉ የካንሰር አይነቶች መካከል የሳምባ፣ የሽንት ቧንቧ፣ አንጀት፣ ማህጸን፣ ጡት፣ ጉበት እና ጣፊያ ካንሰሮች ዋነኞቹ ናቸውም ተብሏል፡፡
ከዚህ በፊት ካንሰር በእድሜ የገፉ ሰዎችን የበለጠ ያጠቃል ቢባልም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን ወጣቶች የበለጠ እየተጠቁ እንደሆነ በጥናቱ ለይ ተጠቅሷል፡፡
ስብ የበዛባቸው ምግቦችን መመገብ፣ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ አለማድረግ፣ የኬሚካል ብክለት፣ በቂ አንቅልፍ አለማግኘት እና የተቀነባበሩ ምግቦችን አዘውትሮ መመገብ ለካንሰር በሽታ አጋላጭ ምክንያቶች እንደሆኑም በጥናቱ ለይ ተገልጿል፡፡