ሩሲያ የካንሰር ክትባት ለማግኘት መቃረቧን ፑቲን ገለጹ
የሩሲያ ተመራማሪዎች በቅርቡ ለታካሚዎች ሊሰጡ የሚችሉ የካንሰር ክትባቶችን ለመፍጠር ተቃርበዋል ብለዋል
ፕሬዝዳንት ፑቲን ክትባቶቹ ለየትኛው የካንሰር አይነት እንደሚሰሩ ለይተው አላስቀመጡም
ሩሲያ የካንሰር ክትባት ለማግኘት መቃረቧን የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን አስታወቁ።
ፕሬዝዳንት ፑቲን ባሳለፍነው ረቡዕ እንደተናገሩት፤ የሩሲያ ተመራማሪዎች በቅርቡ ለታካዎች መሰጠት የሚችል የካንሰር ክትባት እውን ለማድረግ ተቃርበዋል።
ፑቲን በቴሌቭዥን በተሰጡት አስተያየት "የካንሰር ክትባቶች እና የአዲሱ ትውልድ የበሽታ መከላከያ መድሃኒቶችን ለመፍጠር በጣም ተቃርበናል" ብለዋል።
“ክትባቶቹ እና መድሃቶቹ በቅርቡ እንደ ለግለሰብ በሚደረጉ ሕክምናዎች ውጤታማ በሆነ መንገድ ጥቅም ላይ እንደሚውሉ ተስፋ አደርጋለሁ” ሲሉም ፑቲን ተናግረዋል።
ፕሬዝዳንት ፑቲን ክትባቶቹ ለየትኛው የካንሰር አይነት እንደሚውሉ እና እንዴት እንደሚሰሩ ለይተው አላስቀመጡም ነው የተባለው።
በርካታ ሀገራት እና ኩባንያዎች ለካሰር መከላከያ ክትባት ለመስራት ጥረት በማድረግ ላይ መሆናቸው ይታወቃል።
በሳለፍነው ዓመት የብሪታኒያ መንግስት ከጀርመኑ ባዮኤንቴክ ኩባያ ጋር የተፈራረመ ሲሆን፤ ይህም በፈረንጆቹ 2030 ለ10 ሺህ ታካሚዎች የሚደረርስ የግል የካንሰር ህክምናዎች ላይ የክሊኒካ ሙከራ ለማድረግ የሚያስችል ነው ተብሏል።
ሞደሬና እና ኬርክ ኮ የተባሉ የፋርማቲኳል ኩባንያዎችም በቆዳ ካንሰር ሊከሰት የሚችል ካንሰርን መከላከል የሚችል ክትባት ማግኘታቸው ይታወሳል።
በአሁኑ ወቅት የማህጸን በር ጫፍ ካንሰርን ጨምሮ በሰው ልጅ ላይ ካንሰርን የሚያስከትሉ በሂዩማን ፓፒሎማ ቫይረስ (HPV) የሚከላሉ እውቅና የተሰጣቸው ስድስት ክትባቶች እንዳሉ የዓለም ጤና ድርጅት አስታውቋል።