የቀድሞው ፖሊስ ቻውቪን በአሰቃቂ ግድያ ወንጀል ጥፋተኛ ተብሎ የ22 ዓመት እስር ተፈርዶበታል
በጆርጅ ፍሎይድ ግድያ ምክንያት ታስሮ የነበረው ፖሊስ በእስር ቤት መወጋቱ ተገለጸ፡፡
በአሜሪካ ሚኒያፖሊስ ግዛት ነዋሪ የሆነው ጆርጅ ፍሎይድ 20 ዶላር አጭበርብርሃል በሚል ነበር በፖሊስ በቁጥጥር ስር የዋለው፡፡
ዴሪክ ቻውቪን እና ሌሎች የስራ ባልደረቦቹም ፍሎይድን ከያዙ በኋላ ቻውቪን የተባለው ፖሊስ ፖሊስ በእጁ ላይ ካቴና ካሰረ በኋላ በአንገቱ ላይ በጉልበቱ በመቆም ትንፋሽ አጥሮት እንዲሞት አድርጎታል፡፡
ከሶስት ዓመት በፊት የተፈጸመው ይህ ክስተት አሁን ላይ ድርጊቱን የፈጸመው ቻውቪን የ22 ዓመት እስር ተላልፎበት የእስር ጊዜውን እየፈጸመ እያለ የግድያ ሙከራ እንደተደረገበት ተገልጿል፡፡
እንደ ኤፒ ዘገባ ቻውቪን በአሪዞና የፌደራል ማረሚጠያ ቤት ውስጥ በስለታማ ቁስ በተፈጸመበት ጥቃት ልፉኛ ቆስሎ በህክምና ላይ ይገኛል፡፡
86 የአሜሪካ ፖሊሶች ራሳቸውን ማጥፋታቸው ተገለጸ
የ47 ዓመቱ የቀድሞ ፖሊስ ላይ ማን የግድያ ሙከራ እንደፈጸመበት እስካሁን ይፋ ያልተደረገ ሲሆን ጥቃቱ ከጆርጅ ፍሎይድ ግድያ ጋር ይገኛኝ አይገናኝ እስካሁን አልታወቀም፡፡
ማረሚያ ቤቱ በበኩሉ አንድ ታራሚ ላይ በስለት የመውጋት ጥቃት እንደተፈጸመበት ገልጾ የህይወት አድን ህክምና እንደተደረገለት እና ለተጨማሪ ህክምና ወደ ሆስፒታል መወሰዱን አስታውቋል፡፡
ለጆርጅ ፍሎይድ መሞት መንስኤ የሆነው ከአንድ ሱቅ በሀሰተኛ የ20 ዶላር ሲጋራ ገዝቷል በሚል ሲሆን ፖሊሶች በወሰዱት ያለተመጣጠነ እና የተጋነነ ሀይል መጠቀም ምክንያት በአሰቃቂ ሁኔታ ህይወቱ ሊያልፍ ችሏል፡፡
የዚህ ጥቁር አሜሪካዊ ግድያን ተከትሎ በመላው ዓለም በጥቁር ህዝቦች ላይ የሚደርሱ የዘረኝነት ጥቃቶችን የሚቃወሙ ሰላማዊ ሰልፎች ሲካሄዱ ቆይተዋል፡፡