አሜሪካ አዲስ ጉልበት ያለው መሪ እንደምትፈልግ አርኖልድ ሸዋዚንገር ተናገሩ
በ2024 ለሚካሄደው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ዋና እጩዎች የሆኑት ፕሬዝዳንት ባይደን እና ትራምፕ ደክመዋል ተብሏል
የቀድሞው የካሊፎርኒያ አስተዳዳሪ ሸዋዚንግር አሜሪካዊያን ሀገራቸውን ከውስብስብ ችግሮች ነጻ የሚያወጣቸው አዲስ ፕሬዝዳንት እንደሚፈልጉ ተናግረዋል
አሜሪካ አዲስ ጉልበት ያለው መሪ እንደምትፈልግ አርኖልድ ሸዋዚንገር ተናገሩ።
የቀድሞው ተዋናይ እና የካሊፎርኒያ ገዢ የነበሩት አርኖልድ ሸዋዚንገር ስለ ቀጣዩ የአሜሪካ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ከፖለቲኮ ጋዜጣ ጋር ቆይታ ተናግረዋል ።
ሸዋዚንገር እንዳለው ከሆነ አሜሪካ አዲስ ጉልበት ያለው ፕሬዝደንት የምትፈልግበት ወቅት ነው ብለዋል።
በ2024 በሚካሄደው ፕሬዝዳንታዊ ፓርቲ ዶናልድ ትራምፕ እና የወቅቱ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ፓርቲዎቻቸውን ወክለው ለመወዳደር የመጨረሻ ፉክክር ውስጥ ናቸው።
አርኖልድ ሸዋዚንገር እንዳሉት አሜሪካ ውስብስብ ችግሮች እንዳሉባት እና እነዚህንም ችግሮች ለመፍታት አዲስ ፕሬዝዳንት እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል።
እንደ አርኖልድ ሸዋዚንገር ገለጻ ዶናልድ ትራምፕም ሆነ ጆ ባይደን በእድሜ የገፉ በመሆናቸው ችግሮችን መፍታት እሚችሉበት ወቅት ላይም አይደሉም።
በስልጣን ላይ ያሉት ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን አሁን ላይ 80ኛ ዓመታቸው ላይ ሲሆኑ ዶናልድ ትራምፕ ደግሞ 77ኛ ዓመት ላይ ናቸው።
የዓለማችን ልዕለ ሀያል ሀገር የሆነችው አሜሪካንን ከ2024 ጀምሮ ባሉት አራት ዓመታት ውስጥ በፕሬዝዳንት ለመምራት እጩዎች በቅስቀሳ ወቅት ላይ ሲሆኑ ዶናልድ ትራምፕ እና በስልጣን ላይ ያሉት ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ዋነኛ ተፎካካሪዎች እንደሚሆኑ ይጠበቃል።