ጥቅሟን የማያስጠብቅ አንድ ቃል ከተካተተ ኢትዮጵያ ስምምነቱን አትፈርምም
ጥቅሟን የማያስጠብቅ አንድ ቃል ከተካተተ ኢትዮጵያ ስምምነቱን አትፈርምም
የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ድርድር የኢትዮጵያን ጥቅም በሚያስጠብቅ መልኩ እየተካሄደ እንደሚገኝ የውሃ፣ መስኖ እና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ዶ/ር ኢ/ር ስለሺ በቀለ ገልጸዋል፡፡
ሚኒስትሩ ከግብጽ እና ሱዳን ጋር በአሜሪካ ሲደረግ የነበረውን ድርድር አስመልክተው ዛሬ ጋዜጣዊ መግለጫን ሰጥተዋል፡፡
በመግለጫቸውም የግድቡን የውኃ ሙሌትና አለቃቀቅ አስመልክተው በቀረቡ አራት የተለያዩ ሰነዶች ላይ የሦስቱን ሀገራት ጥቅም በሚያስጠብቅ መልኩ የአሜሪካና የአለም ባንክ ታዘቢዎች በተገኙበት ውጤታማ ድርድር መደረጉን አስታውቀዋል፡፡
በቴክኒካዊ፣ በህጋዊ፤ በግጭት አፈታት እና በትብብር ጉዳዮች ላይ የኢትዮጵያን ጥቅም በሚያስከብር መልኩ ስምምነት ላይ ከተደረሰ በአጭር ጊዜ መፈራረም እንችላለን ሲሉም ነው ሚኒስትሩ የተናገሩት፡፡
ወደፊትም ቢሆን የመጠቀም መብቷን በዘላቂነት በማያስጠብቅ ሁኔታ አንድም ቃል ከተካተተ ኢትዮጵያ እንደማትፈርም ሚኒስትሩ አበክረው ገልጸዋል፡፡
በመጨረሻም የኢትዮጵያ ጥቅም ተላልፎ እንደተሰጠ በማስመሰል በማህበራዊ ሚዲያ ላይ የሚናፈሰው ወሬ ትክክል እንዳልሆነ እና የህግ አማካሪዎቻችን የካበተ ልምድ ያላቸው በመሆኑ እንደ ከዚህ በፊቱ ውሃው የኛ ብቻ ነው የሚለው አስተሳሰብ ተቀባይነት የለውም ብለዋል፡፡