የጀርመን ፍርድ ቤት በቀድሞ የናዚ ካምፕ ጸኃፊ ላይ ተላልፎ የነበረውን ፍርድ አጸና
ፍርድ ቤቱ ሴትዮዋ እንደ ጸኃፊ የቀን ተቀን ተግባራትን ከማከናውን ያለፈ ተሳትፎ አልነበራቸውም የሚለውን የጠበቃውን መከራከሪያ ውድቅ አድርጎታል
የክስ ሂደታቸው ሲጀመር ፍርድ ቤት ያልቀረቡት ፈርችነር፣ ዳኞች የእስር ማዛዣ ካወጡባቸው የአለም አዛውንት ሴቶች አንዷ ሆነዋል
የጀርመን ፍርድ ቤት በቀድሞ የናዚ ካምፕ ጸኃፊ ላይ አስተላልፎት የነበረውን ፍርድ አጸና።
የጀርመን ፌደራል ፍርድ ቤት በሁለተኛው የአለም ጦርነት የመጨረዎቹ ሁለት አመታት ውስጥ በናዚ ካምፕ በጸኃፊነት ሲሰሩ የነበሩት የ99 አመት ሴት ለግድያ አስተዋጽኦ አድርዋል በሚል ተላልፎባቸው የነበረውን የጥፋተኝነት ውሳኔ አጽንቶታል።
ኢርምጋርድ ፈርችነር የተባሉት እኝህ ሴት በ19 አመታቸው ስተትሆፍ በተባለው የናዚ ማከማቻ ካምፕ በጸኃፊነት በሰሩበት ወቅት ከ10ሺ በላይ ሰዎች እንዲገደሉ በመርዳት እና በማበረታታት ተከሰው በፈረንጆቹ 2022 ለሁለት አመታት የሚቆይ የገደብ ቅጣት ተላልፎባቸው ነበር።
ፍርድ ቤቱ የሴትዮዋ እንደ ጸኃፊ የቀን ተቀን ተግባራትን ከማከናውን ያለፈ ተሳትፎ አልነበራቸውም የሚለውን የጠበቃውን መከራከሪያ ውድቅ አድርጎታል።
ፍርድ ቤቱ የታችኛው ፍርድ ቤት ያስተላለፈውን ውሳኔ በማጽናት የመጨረሻ ውሳኔ ሰጥቷል፤ ከዚህ በኋላ ይግባኝ የሚጠየቅበትም አይሆንም።
"ተከሳሿ ዋና አጥፊዎች ምን እየሰሩ እንደነበር እያወቁ እና ስራቸውን እየደገፉ፣ ሙያዊ ስራ ነበር የምስራው የሚለው መርህ እዚህ ላይ አይሰራም" ሲሉ የሊፕዚንግ ፍርድ ቤት ዳኞች ተናግረዋል።
በግዳንስክ አቅራቢያ በሚገኘው ስተትሆፍ በሚገኘው የጋዝ ክፍል ቢያንስ 65ሺ ሰዎች በረሀብ ወይም በበሽታ ሞተዋል። ከእነዚህ ውስጥ የጦር ምርኮኞች እና በናዚ የዘር ማጥፋት ዘመቻ የተያዙ አይሁዶች ይገኙበታል። አብዛኞቹ በጋዝ እንዲጠቁ ወደ አስቺውትዝ ካምፕ እንዲላኩ ይደረግ ነበር።
በፈረንጆቹ 2021 የክስ ሂደታቸው ሲጀመር ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ የቀሩት የ96 አመቷ ፈርችነር፣ ዳኞች የእስር ማዛዣ ካወጡባቸው የአለም አዛውንት ሴቶች አንዷ ሆነዋል።
በሁለኛው የአለም ጦርነት ወቅት በአይሁዶች ላይ በተፈጸመው ዘግናኝ የዘር ማጥፋት ወንጀል ተሳትፎ የነበራቸው ግለሰቦች ተፈልገው እየተያዙ ለፍርድ እየቀረቡ ናቸው።
በአውሮፖ በተለይ በጀርመን በተፈጸመው ጸረ-አይሁድ ጥቃት ቢንያስ ስድስት ሚሊዮን አይሁዶች ተጨፍጭፈዋል።