ስኮትላንድ ሁሉንም አይነት እጽ መጠቀምን ህጋዊ ለማድረግ ሀሳብ አቀረበች
አደንዛዥ እጽ ተጠቃሚዎችን በወንጀል ከመጠየቅ ይልቅ እንዲታከሙና እንዲደግፉ የሚያስችል ነው
ብሪታኒያ በመድኃኒት ላይ ያለኝን ጠንካራ አቋም ለመቀየር ምንም አይነት ዕቅድ የለኝም ብላለች
ስኮትላንድ በአውሮፓ አስከፊውን የመድኃኒት ሞት መጠን ለመቋቋም ሁሉንም ለግል ጥቅም የሚውሉ እጾችን ህጋዊ ለማድረግ ወጥናለች።
በኤድንበርግ የተወከለው መንግስት እንደዚህ አይነት ውሳኔዎችን በሚያሳልፈው በእንግሊዝ መንግስት ህጉ መጽደቅ አለበት ብሏል።
እርምጃው ችግር ያለባቸው አደንዛዥ እጽ ተጠቃሚዎችን በወንጀል ከመጠየቅ ይልቅ እንዲታከሙ እና እንዲደግፉ የሚያስችል ነው።
በማገገም ላይ ያሉትን ደግሞ ስራ የማግኘት እድል እንደሚፈጥር ተናግሯል።
የስኮትላንድ የመድኃኒት ፖሊሲ ሚንስትር ኢሌና ዊትሃም በሰጡት መግለጫ "እነዚህ ሀሳቦች ክርክር እንደሚያስነሱ ብናውቅም ከህዝብ ጤና እይታችን ጋር የሚጣጣሙ፣ ብሄራዊ ተልእኳችንን ለማሻሻል እና ህይወትን ለማዳን ይጠቅማሉ" ብለዋል።
"የመድኃኒት ሞትን ለመቀነስ ባለን አቅም ጠንክረን እየሰራን ነው። እና ብዙ ማድረግ ያለብን ቢሆንም አካሄዳችን በቀላሉ ከምንሰራው የዌስትሚኒስተር ህግ ጋር የሚጋጭ ነው" በማለት የማሻሻያውን አስፈላጊነት አንስተዋል።
የብሪታኒያ ጠቅላይ ሚንስትር ሪሺ ሱናክ ቃል አቀባይ "በመድኃኒት ላይ ያለንን ጠንካራ አቋም ለመቀየር ምንም አይነት እቅድ የለም" ሲሉ ለውጥ እንደሌለ ገልጸዋል።
ስኮትላንድ ነጻ ሀገር እንድትሆን የሚፈልገው ገዥው የስኮትላንድ ብሄራዊ ፓርቲ፤ ከብሪታንያ መንግስት ጋር ፍጥጫ ውስጥ ገብቷል።
ከአንድ ሚሊዮን ህዝብ 327 ሰዎች በእጽ ምክንያት የሚሞቱባት ስኮትላንድ፤ በአውሮፓ ከፍተኛው የአደንዛዥ እጽ ሞት መጠን አላት።