ጀርመን የነዳጅ ዋጋን ለማረጋጋት 200 ቢሊዮን ዩሮ መደበች
ብሪታንያም በተመሳሳይ ለነዳጅ ድጎማ 150 ቢሊዮን ዩሮ ለመመድብ በሂደት ላይ ትገኛለች
ብሪታንያም በተመሳሳይ ለነዳጅ ድጎማ 150 ቢሊዮን ዩሮ ለመመድብ በሂደት ላይ ትገኛለች
የሩሲያ እና ዩክሬን ጦርነትን ተከትሎ ምዕራባውያን ሀገራት በሞስኮ ነዳጅ ላይ ማዕቀብ ጥለዋል።
ማዕቀቡ 40 በመቶ የአውሮፓን ነዳጅ ፍላጎት ስታሟላ የቆየችው ሩሲያ ለአውሮፓ ማቅረብ ያልቻለች ሲሆን ይህም በአውሮፓ የኢኮኖሚ አለመረጋጋት እንዲፈጠር አድርጓል።
የነዳጅ ፍላጎቷን ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ ከሩሲያ ስትገዛ የነበረችው ጀርመን ዋነኛ ተጎጂ ሀገር ሆናለች።
አምራች ኢንዱስትሪዎች፣ የአቪዬሽን ሰራተኞች እና የትራንስፖርት አገልግሎት ተጠቃሚ ማህበረሰብ በነዳጅ ዋጋ መጨመር እየተፈተኑ እንደሆነ ሮይተርስ ዘግቧል።
ይሄንንም ተከትሎ ሰራተኞች መንግስት የኢኮኖሚ ማሻሻያ እርምጃዎችን እንሲወስድ በስራ ማቆም አድማ እና ሌሎች መንገዶች በመጠየቅ ላይም ናቸው።
የጀርመን መንግስትም የነዳጅ ድጎማ ለማድረግ 200 ቢሊዮን ዩሮ እንደሚመድብ አስታውቋል።
የጀርመን መራሄ መንግስት ኦላፍ ሾልዝ እንዳሉት የነዳጅ ዋጋን ዝቅ ለማድረግ መንግስታቸው ድጎማ እንደሚያቀርብ ተናግረዋል።
እንደ ኦላፍ ሾልዝ ገለጻ የነዳጅ ድጎማው ለቀጣዮቹ ሁለት ዓመታት ይቀጥላል የተባለ ሲሆን በጀቱን የሀገሪቱ መንግስት በብድር ይሸፍናልም ተብሏል።
በተመሳሳይም ብሪታንያ የነዳጅ ዋጋን ለማረጋጋት የነዳጅ ድጎማ እንደምታደርግ አስታውቃለች።
ብሪታንያ ለዚሁ የነዳጅ ድጎማ 150 ቢሊዮን ዩሮ ለመመደብ እንቅስቃሴ ላይ እንደሆነች ተገልጿል።
በፈረንሳይ በትናንትናው ዕለት በዋና ከተማዋ ፓሪስን ጨምሮ በሌሎች የሀገሪቱ ከተሞች መምህራን ፣ የባቡር ትራንስፖርት እና ሌሎች ተቋማት ሰራተኞች የፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን መንግስት ለኑሮ ውድነቱ ድጎማ እንዲያደርግ በሰላማዊ ሰልፍ ጠይቀዋል።