ጠ/ሚኒስትር ኔታንያሁ “በግጭት ውስጥ የተሳተፉ የኤርትራ ስደተኞች በአስቸኳይ እንዲባረሩ እፈልጋለሁ” አሉ
አፍሪካውያን ስደተኞች በሙሉ ከእስራኤል ለማሰወጣት የሚያስችል እቅድ እንዲዘጋጅ ኔታንያሁ አዘዋል
በእስራኤል በሚኖሩ የኤርትራ ጥገኝነት ጠያቂዎች መካከል በተከሰተ ግጭት ከ160 በላይ ሰዎች ተጎድተዋል
የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ በትናትናው እለት በቴል አቪቭ በተከሰተው ግጭት ውስጥ የተሳተፉ ኤርትራውያን ስደተኞች በአስቸኳይ ከሀገሪቱ እንዲባረሩ ፍላጎት እንዳላቸው ገለጹ።
በእስራኤል ቴል አቪቭ በመኒኖሩ ኤርትራውያን መካከል በትናንትናው እለት በተቀሰቀሰው ግጭት በትንሹ 160 ሰዎች መጎዳታቸው ተሰምቷል።
በግጭቱ ጉዳት ከደረሰባቸው ሰዎች መካከል ቢያንስ ስምንት ኤርትራውያን ስደተኞች ከፖሊስ በተተኮሰ ጥይት ተመተው ከፍተኛ ጉዳት እንደደረሰባቸው የተገለፀ ሲሆን፤ 50 የእስራኤል ፖሊስ አባላትም መጎዳታቸው ተገልጿል።
- በእስራኤል በሚኖሩ የኤርትራ ጥገኝነት ጠያቂዎች መካከል በተከሰተ ግጭት ከ160 በላይ ሰዎች ተጎድተዋል
- ኤርትራዊያን በስዊድን ስቶኮለም ጎራ ከፍለው መደባደባቸው ተገለጸ
ግጭቱ የተቀሰቀሰው በቴል አቪቭ የኤርትራ ኤምባሲ ያዘጋጀውን ዝግጅት በመቃወም የወጡ በመቶ የሚቆጠሩ ጥገኝነት ጠያቂ ኤርትራውያን ከፖሊስ ጋር ተጋጭተው እንደሆነም ጄሩሳሌም ፖስት ዘግቧል።
የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ በትናንትናው እለት ኤርትራውያን ጥገኘነት ጠያቂዎች ባስነሱት ረብሻ ዙሪያ በዛሬው እለት ከሚኒስትሮች ግብረ ኃይል ጋር አስቸኳይ ስብሰባ ተቀምጠዋል።
በስብሰባው ወቅትም ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ በትናትናው እለት በቴል አቪቭ በተከሰተው ሁከት ውስጥ የተሳተፉ ኤርታረውያን ስደተኞች በአስቸኳይ ከሀገሪቱ እንዲባረሩ እንደሚፈልጉ አስታውቀዋል።
በተጨማሪም በእስራዔል የሚገኙ አፍሪካውያን ስደተኞች ከእስራዔል ማስወጣት የሚያስችል እቅድ እንዲዘጋጅ ማዘዛቸውንም ኤ.ፒ ዘግቧል።
ኔታንያሁ በስብሰባው ላይ ባደረጉት ንግግር፤ በአመጸኞች ላይ ወደ መጡበት ሀገራቸው መመለስን ጨምሮ ከበድ ላይ እርምጃ እንዲወሰድ እንፈልጋለን ብለዋል።
በእስራዔል ከ25 ሺህ በላይ አፍሪካውያን ስደተኞች የሚገኙ ሲሆን፤ ከአነዚህም መካከል አብዛኞቹ ኤርትራውያን እና ሱዳናውያን ናቸው፤ እነዚህ ስደተኞች ግጭት እና ጭቆናን በመሸሽ ወደ እስራዔል እንደሸሹም ይናገራሉ።
እስራኤል ለጥቂቶቹን ጥገኝነት ጠያቂዎች ብቻ እውቅና የትምሰጥ ሲሆን፤ አብዛኞቹን እንደ ኢኮኖሚያዊ ስደተኛ አድርገው በማየቷ እነሱን የመጠበቅ ህጋዊ ግዴታ እንደሌለባት ተናግራለች።