ሕንድ በቀጣዮቹ ሁለት ዓመታት ውስጥ ከጃፓን እና ጀርመን የተሸለ ኢኮኖሚ እንደሚኖራት ተገምቷል
ጃፓን የዓለም ኢኮኖሚ ደረጃዋን በጀርመን ተነጠቀች፡፡
ላለፉት አስርት ዓመታት ከቻይና በመቀጠል የዓለማችን ሶስተኛ ግዙፍ ኢኮኖሚ ባለቤት የነበረችው ጃፓን ደረጃዋን በጀርመን ተነጥቃለች፡፡
ጃፓን በ2023 ዓመት ዓመታዊ እድገቷ 4 ነጥብ 2 ትሪሊዮን ዶላር የነበረ ሲሆን የጀርመን ደግሞ 4 ነጥብ 5 ትሮሊዮን ዶላር መሆኑን ተከትሎ የደረጃ ለውጥ አድርገዋል ተብሏል፡፡
ጃፓን በ1980ዎቹ የነበራት የኢኮኖሚ ግስጋሴ ዓለምን ኢኮኖሚ ትቆጣጠራለች ተብላ ተጠብቃ የነበረ ቢሆንም በተለያዩ ምክንያቶች ኢኮኖሚዋ የታሰበውን ያል ርቀት መጓዝ አልቻለም፡፡
ጎረቤቷ ቻይና በ1980ዎቹ በብዙ እጥፍ ያነሰ ኢኮኖሚ የነበራት ቢሆንም ዛሬ ላይ የቻይና ኢኮኖሚ ከጃፓን አራት እጥፍ የተሻለ ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡
ከጃፓን ብዙ የተሻለ እድል የሌላት ጀርመንም ከ2027 ጀምሮ ደረጃዋን በሕንድ ልትነጠቅ እንደምትችል የአይኤምኤፍ ትንበያ ያስረዳል፡፡
የህዝብ ቁጥር ማሽቆልቆል፣ የዋጋ ግሽበት፣ የየን ምንዛሬ በዶላር እና በቻይናው ዩዋን መበለጥ እና የዓለም ኢኮኖሚ መለዋወጥ ለጃፓን ኢኮኖሚ መጎዳት ዋነኛ ምክንያቶች እንደሆኑ ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
የጃፓን ኢኮኖሚ ምርቶችን ወደ ውጭ ሀገራት በመላክ ላይ የተመሰረተ ሲሆን ኩባንያዎች ምርቶቻቸውን ወደ ውጭ ሲልኩ የሀገሪቱ መገበያያ ገንዘብ የን መርከሱን ተከትሎ የቻይና እና ህንድ ኩባንያዎች የገበያ ብልጫ ወስደውባታልም ተብሏል፡፡
ከምግብና መጠጥ ጋር ጥፊ የሚያቀርበው የጃፓን መጠጥ ቤት
ጃፓን ኢኮኖሚዋን ለመታደግ የተለያዩ እርምጃዎችን መውሰድ ካልቻለች ኢኮኖሚዋ የባሰ እየተጎዳ ሊሄድ እንደሚችልም ተሰግቷል፡፡
የአውሮፓ ባለግዙፍ ኢኮኖሚዋ ጀርመንም የኢኮኖሚ እድገቷ አጥጋቢ እንዳልሆነ የተገለጸ ሲሆን የሰራተኞች እጥረት፣ የሀይል ዋጋ መናር እና የአውሮፓ ህብረት የጣላቸው የግብር ህጎች ኢኮኖሚዋን እየጎዱባት ነውም ተብሏል፡፡