ፕሬዝዳንት ዘሌንስኪ የፕሬዝዳንት ፍራንክ ዋልተር ስቴይንሜይርን የኪቭ ጉብኝት ውድቅ አድርገዋል
ዩክሬን የጀርመን ፕሬዝዳንት እንዲጎበኟት ሳትፈቅድ ቀረች፡፡
ፕሬዝዳንት ፍራንክ ዋልተር ስቴይንሜይር ኪቭን ለመጎብኘት ፍላጎት ቢኖራቸውም ከዩክሬን ባለስልጣናት ፈቃድ ሳያገኙ ቀርተዋል ተብሏል፡፡
ይህንምም "ኪቭ አልፈለገችኝም" ያሉት ፕሬዝዳንት ፍራንክ ዋልተር ስቴይንሜይር ተናግረዋል፡፡
የ66 ዓመቱ አዛውንት ከፖላንድ ፕሬዝዳንት አንድሬ ዱዳ እና ኬሎች ከኢስቶኒያ፣ ላቲቪያ እና ሉትዋኒያ ፕሬዝዳንቶች ጋር ነበር ወደ ኪቭ ለማቅናት ያሰቡት፡፡
ሆኖም ኪቭ በእርሳቸው ደስተኛ አለመሆኗን ተከትሎ የጉብኝት እቅዳቸው ሳይሳካ ቀርቷል፡፡ በእርግጥ እነ አንድሬ ዱዳን ያካተተው የአውሮፓ ህብረት ልዑክ ኪቭን ሊጎበኝ ስለመቻሉም የታወቀ ነገር የለም፡፡
የዩክሬን ፕሬዝዳንት ቮሎዶሚር ዘሌንስኪ ዋልተር ስቴይንሜይር ከሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር ባላቸው ግንኙነት ደስተኛ አይደሉም፡፡ ሩሲያ ኖርድ ስትሪም 2 የተባለ ሁለተኛ የነዳጅ ማስተላለፊያ ቱቦ በጀርመን መገንባቷን መደገፋቸውንም ዜሌንስኪ ተችተዋል፡፡ ይህን ተከትሎም ነው አዛውንቱ ኪቭን እንዳይጎበኙ የከለከሉት፡፡
የዩክሬን ፕሬዝዳንት በአፍሪካ ህብረት ንግግር ለማድረግ ጠየቁ
ስቴይንሜይር የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ከአሁን ቀደም ልክ በጦርነቱ እንደተስተዋለው "ደም" የጠማው እንዳልነበር በመግለጽም ከዩክሬን ጎን መቆሜ የሚያወላዳ አይደለም ሲሉ ገልጸው ነበር፡፡ሆኖም ሃሳባቸው ተቀባይነት አላገኘም፡፡
ጀርመን ከጦርነቱ ጋር በተያያዘ እንደ አውሮፓ ህብረት የተወሰዱ የማዕቀብና ሌሎችንም እርምጃዎች ብትደግፍም ከሩሲያ ነዳጅ መግዛቷን ለማቆም ግን አልደፈረችም፡፡