ጣሊያን በሩሲያ ላይ ካላት የነዳጅ ጥገኝነት ለመላቀቅ አፍሪካን እያማተረች ነው
ጣሊያን 45 በመቶ ያህል የነዳጅ ፍላጎቷን የምታሟላው ከሩሲያ ነው 95 በመቶ የጣሊያን የነዳጅ ፍላጎቷን ከውጭ
የሃገሪቱ ባለስልጣናት ነዳጅ ፍለጋ ወደ ማዕከላዊ አፍሪካ ማቅናታቸው ተሰምቷል
ጣሊያን በሩሲያ ላይ ካላት የነዳጅ ጥገኝነት ለመላቀቅ አፍሪካን ተስፋ አድርጋለች ተባለ፡፡
የሃገሪቱ ከፍተኛ ባለስልጣናት የአፍሪካን የነዳጅ አቅም በማማተር ላይ መሆናቸው ተነግሯል፡፡
ምዕራባውያን የሩሲያ ነዳጅ ላይ ማዕቀብ ከጣሉ በዓለም ገበያ ላይ ያልተጠበቀ አደጋ ያስከትላል ስትል ሩሲያ አስጠነቀቀች
አስቸኳይ የነዳጅ ገበያን ያገኙ ዘንድ ሚኒስትሮቿን ወደ ማዕከላዊ አፍሪካ መላኳም ነው የተነገረው፡፡ አንጎላ እና ኮንጎ ሪፐብሊክን በነዳጅ ግብይት አማራጭ አጋር ለማድረግ ስለማሰቧም ተሰምቷል፡፡
ጣሊያን 45 በመቶ ያህል የነዳጅ ፍላጎቷን የምታሟላው ከሩሲያ ነው፡፡ ይህም በሩሲያ ነዳጅ ላይ ጥገኛ ከሆኑ ጀርመንን መሰል የአውሮፓ ሃገራት አንዷ አድርጓታል፡፡ በዩክሬን ጦርነት ጉዳይ የራሷን አቋም ለማራመድ እንዳላስቻላትም ነው የተነገረው፡፡
አሁን ግን ከሩሲያ ጥገኝነት ለመላቀቅ አጥብቃ ትፈልጋለች፡፡ ምጣኔ ሃብታዊ ጥገኝነት ለፖለቲካ መጠቀሚያ መሆን አይገባውም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ማሪዮ ድራጊ በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዲ ማዮ የተመራ ልዑክ ወደ ማዕከላዊ አፍሪካ ልከዋል፡፡
የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚኒስትር ነዳጅ ፍለጋ የገልፍ ሃገራትን መዞር ጀመሩ
ጣሊያን ከአሁን ቀደምም ተጨማሪ ነዳጅን እንድታቀርብላት ከአልጄሪያ እንዲሁም ከግብጽ ጋር ስምምነት አድርጋለች፡፡ ከሩሲያ በመቀጠል ለጣሊያን ከፍተኛ ነዳጅን የምታቀርበው አልጄሪያ ናት፡፡ 30 በመቶ ያህል ፍጆታዋን የምትሸፍነውም አልጄሪያ ነች፡፡
45 በመቶ ያህሉ የጣሊያን የኢነርጂ ፍጆታ በነዳጅ የሚሸፈን ነው፡፡ 95 በመቶ ያህሉ የነዳጅ አቅርቦትም ከውጭ የሚገባ ነው፡፡