ጀርመን ስደተኞችን በመጠቀም የህዝብ ብዛቷን ማሳደግ እንደምትፈልግ ገለጸች
ጀርመን የህዝብ ብዛቷን ወደ 90 ሚሊዮን ከፍ የማድረግ እቅድ እንዳላት አስታውቃለች
ጀርመን በተለይም የሰራተኞችን ቁጥር ለማሳደግ ስደተኞችን እንደ አማራጭ እንደምትጠቀም ገልጻለች
ጀርመን ስደተኞችን በመጠቀም የህዝብ ብዛቷን ማሳደግ እንደምትፈልግ ገለጸች።
የጀርመን መንግስት የፍልሰት ህግን ለማሻሻል ያለውን እቅድ ባለፈው ወር ይፋ አድርጓል።
እርጅና ያለው የህዝብ ቁጥር በጀርመን መንግስት የጡረታ ስርዓት ላይ ጫና እየፈጠረ ነው ተብሏል።
የጀርመን ቻንስለር ኦላፍ ሾልስ ጀርመን በቀጣዮቹ ዓመታት ህዝቧን በከፍተኛ ሁኔታ መጨመር እንደምትችል ተናግረዋል። ሀገሪቱ የመንግስት የሰራተኛ እጥረትን እና በጡረታ ስርዓቷ ላይ የሚፈጠረውን ቀውስ ለመከላከል ፍልሰትን ለማሳደግ ጥረት እያደረገች እንደሆነ ገልጸዋል።
ሾልስ በበርሊን አቅራቢያ በፖትስዳም ከተማ በተካሄደው የዜጎች ፎረም እንደተናገሩት ምንም እንኳን ከህዝብ ቁጥሩ ያረጀው የህዝብ ቁጥር ከፍ ቢልም መንግስት የውጭ ሰራተኞችን ለመሳብ እየሰራ ነው።
በፈረንጆቹ 2070 የሚገመተው ሰባት በመቶ የህዝብ ቁጥር እድገት የጀርመንን ህዝብ ወደ 90 ሚሊዮን ከፍ ያደርገዋል ተብሏል።
የአውሮፓ ትልቁ ኢኮኖሚ በሆነችው በርሊን ውስጥ ከአውሮፓ ህብረት ውጭ ለሚመጡና ፍላጎት ላላቸው ሰራተኞች የስራ ገበያ ለመክፈት እየፈለገች ባለችበት ወቅት የጀርመን መንግስት የፍልሰተኛ ህግን ለማሻሻል ያለውን እቅድ ባለፈው ወር ተስማምቷል።
መንግስት የሀገሪቱ ምጣኔ-ሀብት እድገት እየተዳከመ ባለበት ወቅት የሰው ኃይል እጥረት ለመቅረፍ የፍልሰት ህግን እና ስልጠናን ማሳደግ እንደሚፈልግ ገልጿል።
ያረጀ የህዝብ ቁጥር በመንግስት የጡረታ ስርዓት ላይ ጫና እየፈጠረ ነው ተብሏል።
ሾልስ በአሁኑ ወቅት የህዝብ ቁጥር በከፊል እየጨመረ በመጣው ፍልሰተኛ ምክንያት መንግስት በፈረንጆቹ 2025 ስልጣን ከማጠናቀቁ በፊት የጡረታ መዋጮ ላያሻሽል ይችላል ብለዋል።
የጀርመን ስታስቲክስ ቢሮ ባለፈው ሳምንት የህዝቡ ቁጥር በዚህ ዓመት ከዩክሬን በስደት በመጡ ሰዎች በአንድ ሚሊዮን ከፍ ሊል እንደሚችል የተናገረ ሲሆን፤ ይህም 84 ሚሊዮን የሆነው ጠቅላላ ህዝብ ከፍ እንዲል ያደርጋል ብሏል።
የፍልሰተኛ ቁጥር ከፍ የሚል ከሆነም በሚቀጥሉት አስርት ዓመታት ውስጥ ወደ 90 ሚሊዮን ሊደርስ እንደሚችል አክሏል።