የጀርመኑ መሪ፤ ዓለም በቡድን ተከፋፍላ አዲስ የቀዝቃዛ ጦርነት እንዳይፈጠር አስጠነቀቁ
ኦላፍ ሾልዝ፤ ጀርመን የአውሮፓ ደህንነት ዋስትና ለማረጋገጥ ዝግጁ ናት ብለዋል
ኦላፍ ሾልዝ፤ ቻይናን እና ሩሲያ በዓለም ላይ ስጋት እየፈጠሩ ነው ሲሉ ከሰዋል
የጀርመኑ መራሄ መንግስት ኦላፍ ሾልዝ ዓለም በቡድን ተከፋፍላ አዲስ የቀዝቃዛ ጦርነት እንዳይፈጠር አስጠነቀቁ፡፡
ኦላፍ ሾልዝ ዓለም ርዕዮተ ዓለም ሳያግደው አዲስ አጋርነት ለመመስረት የተቻለውን ሁሉ ጥረት ማድረግ እንዳለበት ማሳሰበቻወም ነው ፎረይን አፈይርስ መጽሄት ሰኞ እለት በኦንላይን ይዞት በወታው ጽሁፉ ላይ ያስነበበው፡፡
ምዕራባውያን ለዴሞክራሲያዊ እሴቶች መቆም አለባቸው፤ "ነገር ግን ዓለምን እንደገና በካምፖች የመከፋፈል ፈተናን ማስወገድ አለብን" ሲሉም ጽፈዋል ሾልዝ።
ሾልዝ በተለይ ቻይናን እና ሩሲያን የኃይል ሚዛን ፉክክር በበዘባት ዓለም ላይ ስጋት የሚፈጥሩ ሁለት ሀገራት በማለት የሰየሟቸው ሲሆን ከሁለቱም ሀገራት የሚቃጣውን አደጋ ለመቋቋም ጠንካራ የአውሮፓ እና ከአትላንቲክ ባሻገር ከሚገኙ ሀገራት አንድነትን ይጠበቃል ብለዋል፡፡
በሩሲያ በአጋር ግዛቶች ላይ ሊደርስ የሚችለውን ጥቃትና ተግዳሮቶች ለመጋፈጥ የትራንስ አትላንቲክ አጋርነት ወሳኝ ነው ያሉት የጀርመኑ መራሄ መንግስት፤ ቻይና በታይዋን ላይ እየተከተለች ያለውን አካሄድ ለመግታትም በተመሳሳይ አውሮፓ እና አሜሪካ ከዓለም ሀገራት ጋር አዲስ እና ጠንካራ አጋርነት መፍጠር ይጠበቅባቸዋል ብለዋል፡፡
አክለውም “አጋሮቻችን እንድንሆን እንደሚፈልጉን ጀርመኖች የአውሮፓ ደህንነት ዋስትና ለማረጋገጥ፣ በአውሮፓ ህብረት ውስጥ ዋና ድልድይ በመሆን ቁልፍ ሚና ለመጫወት እና ለዓለም አቀፍ ችግሮች ሁለገብ መፍትሔዎች ጠበቃ ለመሆን አስበዋል” ብለዋል፡፡
ጀርመን የአውሮፓን ጸጥታ ለመምራት የሚያችላት ግዙፍ ሆነ የታጠቀ ጦር በመገንባት ላይ መሆኗ የሀገሪቱ መሪ በቅርቡ ማስታወቃቸው አይዘነጋም፡፡
ኦላፍ ሾልዝ፤ በሀገሪቱ ከፍተኛ ባለስልጣኖች ፊት ባደረጉት ንግግር "ጀርመን ከፍተኛ የኢኮኖሚ አቅም ያላትና በአህጉሪቱ መሃል ያለች ሀገር እንደመሆኗ፤ ሰራዊታችን በአውሮፓ ውስጥ የመደበኛ መከላከያ የማዕዘን ድንጋይ መሆን አለበት” ሲሉ ተደምጠዋል፡፡
ጀርመን የታጠቀ ጦር ስትገነባ "ለአውሮፓ ደህንነት የመሪነት ሀላፊነት ለመወጣት ዝግጁ መሆኗን በግልጽ እና በታማኝነት እያሳየች ለመሆኑ ማረጋገጫ ነው"ም ነበር ያሉት ኦላፍ ሾልዝ፡፡