ጀርመን ለዩክሬን የሳይበር ጥቃት መከላከል እና የጦር ወንጀል መረጃዎችን ለመሰብሰብ 1 ቢሊዮን ዶላር መደበች
ጀርመን ዩክሬን የሩሲያን ጦር ለመከላከል ታንኮችን ጨምሮ አጥቂ የጦር ሜዳ መሳሪያዎች እንደሚያስፈልጓት ስትገልጽ ቆይታለች
![](https://cdn.al-ain.com/images/2022/11/12/243-111441-germanyallocates_700x400.jpg)
ሩሲያ በቅርቡ የለቀቀቻትን ኬርሶንን ጨምሮ አራት የሚሆኑ የዩክሬን ግዛቶች ወደ ራሷ ግዛት መጠቅለሏን ይፋ አድርጋ ነበር
የጀርመን መንግሥት ዩክሬን በሩሲያ የሚደርስባትን የሳይበር ጥቃት ለመከላል እና የጦር ወንጀለኞችን ማስረጃ ለመሰብሰብ ከቢሊን ዶላር በላይ መመደቧን አስታውቃለች፡፡
የጀመርመን መንግስት ተጨማሪ ያለውን ድጋፍ ለዩክሬን ያደረገው ከፈረንጆቹ 2023 በጀት መሆኑን ሮይተር ዘግቧል፡፡
ይህ ተጨማሪ ድልድል የመጣው ጀርመን ለዩክሬን የምትሰጠውን ወታደራዊ ዕርዳታ ታጠናክር ወይ የሚል ውዝግብ ባላበት ወቅት ነው፡፡ ጀርመን ዩክሬን የሩሲያን ጦር ለመከላከል ታንኮችን ጨምሮ አጥቂ የጦር ሜዳ መሳሪያዎች እንደሚያስፈልጓት ስገልጽ ቆይታለች፡፡
የሩስያ ፕሬዚደንት ቭላድሚር ፑቲን ወረራውን በየካቲት ወር ካዘዙ በኋላ ለዩክሬን ወታደራዊ ድጋፍ እንዲደረግ ሲወተውት ለነበረው ለግሪንስ ድል ነው ሲል ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
ጀርመን ለዩክሬን ሶስተኛዋ ትልቅ ወታደራዊ ለጋሽ ነች፣ ምንም እንኳን የጦር መሳሪያ ማቅረቡ ለዩክሬን ታጣቂ ሀይሎች የጦር ሜዳ ስኬት ወሳኝ ከነበረችው ከአሜሪካ ባትበልጥም፡፡ ድጋፉ ዩክሬን በሩሲያ ስር የነበረችውን ትልቅ ከተማ ኬርሶንን መልሳ እንድትቆጣጠር ረድቷታል ተብሏል፡፡
የፓርላማ ዩክሬን ቡድን ሊቀመንበር የሆኑት ሮቢን ዋጀነር "የዩክሬን በጀት ድጋፍ ከሆነው የጦር መሳሪያ አቅርቦት የላቀ መሆኑን ግልጽ ያደርገዋል" ብለዋል፡፡
ሩሲያ ኔቶ ወደ ዩክሬን እየስፋፋ ነው በሚል በዩክሬን ላይ ጦርነት ከከፈተች ጀምሮ አሜሪካን ጨምሮ ምእራባውያን ሀገራት ለዩክሬን መጠነ ሰፊ ወታደራዊ ድጋፍ ሲያደርጉ ቆይተዋል፡፡
ሩሲያ በቅርቡ የለቀቀቻትን ኬርሶንን ጨምሮ አራት የሚሆኑ የዩክሬን ግዛቶች ህዝበ ውሳኔ በማካሄድ ወደ ራሷ ግዛት መጠቅለሏን ይፋ አድርጋ ነበር፡፡