የሰዎችን ሰርግ በማበላሸት የሚተዳደረው ሰው
ግለሰቡ አንድን ሰርግ ለማበላሸት 550 ዶላር እንደሚከፈለው ገልጿል
ሰርጋቸው የተበላሸባቸው ሙሽሮች አልያም ቤተሰቦቻቸው በጥፊ ከመቱት ደሞ ክፍያው ይጨምራል ተብሏል
የሰዎችን ሰርግ በማበላሸት የሚተዳደረው ሰው
ኤርነስቶ የሚባለው ስፔናዊ የሰዎችን ሰርግ በማበላሸት ሙያ እንደሚተዳደር አስታውቋል፡፡
ይህ ግለሰብ በተለያዩ ምክንያቶች እንዲበላሽ የሚፈልጉት ሰርግ ካለ አለሁላችሁ በሚል ማስታወቂያ ማስነገር መጀመሩን ተከትሎ ደንበኞቹ እየጎረፉለት መሆኑን ተናግሯል፡፡
ለአንድ ሰርግ 550 ዶላር ዋጋ የቆረጠው ይህ ግለሰብ የቀድሞ ፍቅረኛዎ አልያም በማንኛውም ምክንያት እንዲበላሽ የምትፈልጉት ሰርግ ካለ ሙያዩ ነው እንዳታስቡ ብሏል ሲል ኦዲቲ ሴንትራል ዘግቧል፡፡
ፖሊስ አራት ባሎችን ድል ባለ ሰርግ ያገባችውን ሴት አሰረ
እንደ ዘገባው ከሆነ ክፍያውን ከተቀበለ በኋላ የሚያስፈልገው ነገር የሰርጉ ቦታ፣ ቀን እና ሰዓት ብቻ ነው ያለ ሲሆን ሰርጋቸው የተበላሸባቸው ሙሽሮች ወይም ቤተሰቦች በጥፊ ወይም ሌሎች እርምጃዎችን ከወሰዱበት በአንድ ጥፊ 50 ዶላር ተጨማሪ ክፍያ እንደሚያስከፍልም አስታውቋል፡፡
በተቻለኝ መጠን የተናደዱ ሰዎች እንዳይደርሱብኝ እና እንዳይዙኝ አደርጋለሁ የሚለው ይህ ሰው ነገር ግን ከተያዝኩ እና ከመቱኝ ግን ደንበኛዬ ተጨማሪ ክፍያ የመክፈል ግዴታ ተጥሎበታል ብሏል፡፡
ግለሰቡ ማስታወቂያውን ለቀልድ ብሎ በማህበራዊ ትስስር ገጾች ላይ ያሰራጨው ቢሆንም ፍላጎት ያላቸው ሰዎች ስራውን እንዲገፋበት እንዳደረገውም ተናግሯል፡፡
በዚህም መሰረት እስከ ሕዳር 2 ድረስ በርካታ ትዕዛዛቶችን መቀበሉን ተከትሎ ከተጠቀሰው ቀን በፊት አዲስ ትዕዛዝ መቀበል እንደማይችል አስታውቋል፡፡