ዩ.ኤ.ኢ የኮሮና ቫይረስ መከላከያ ድጋፍ ለአፍሪካ ህብረት አስረከበች
ዩ.ኤ.ኢ ባለፈው ሰኞ እለት 33 ሜትሪክ ቶን የኮሮና ቫይረስ መከላከያ ቁሳቁስ ድጋፍ ወደ ኢትዮጵያ ልካ ነበር
ዩ.ኤ.ኢ ለአፍሪካ ህብረት የተላከውን የኮሮና ቫይረስ መከላከያ የሚሆን የቁሳቁስ ድጋፍ ዛሬ አስረከበች
ዩ.ኤ.ኢ ለአፍሪካ ህብረት የተላከውን የኮሮና ቫይረስ መከላከያ የሚሆን የቁሳቁስ ድጋፍ ዛሬ አስረከበች
የተባበሩት አረብ ኤሚሬትስ (ዩ.ኤ.ኢ) ለአፍሪካ ሀገራት ለኮሮና ቫይረስን መከላከል እንዲውል የላከቸውን የቁሳቁስ ድጋፍ ዛሬ ለአፍሪካ ህብረት አስረክባለች፡፡
በኢትዮጵያ የዩ.ኤ.ኢ አምባሳደር መሀመድ ሳሊም አራሺዲ እርዳታውን ለአፍሪካ ህብረት አስረክበዋል፤ በአፍሪካ ህብረት በኩል እርዳታውን የተቀበሉት በህብረቱ የማህበራዊ ጉዳይ ኮሚሽነር አሚራ ኢልፋዲል ናቸው፡፡
ዩኤ.ኢ. ባለፈው ሰኞ ለኢትዮጵያና ለአፍሪካ የኮሮና ቫይረስ መከላከያ የሚሆን 33 ሜትሪክ ቶን የሚሆን የእርዳታ ቁሳቁስ ልካ ነበር፡፡ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ከዩ.ኤ.ኢ ለኢትዮጵያ ለተላከው ድጋፍ ምስጋና ማቅረባቸው ይታወሳል፡፡
ከተላከው 33ሺ ቶን የድጋፍ ቁሳቁሶችን ውስጥ ለኢትዮጵያ 15 ሜትሪክ ቶን የሚሆነው የድጋፍ ቁሳቁስ ሲበረከት ቀሪው ለአፍሪካ ሀገራት እንደሚበረክት ተገልጾ ነበር፡፡ በዚህ መሰረትም ድጋፉ ዛሬ ለአፍሪካ ህብረት ተሰጥቷል፡፡
ዩ.ኤ.ኢ እየሰጠችው ያለው ድጋፍ የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመግታት የሚደረገውን አለምአቀፍ ጥረት ለማገዝ መሆኑን ገልጿለች፡፡