ጋናዊው ግለሰብ ከ1 ሺህ 100 በላይ ዛፎችን በማቀፍ አዲስ ክብረወሰን አስመዘገበ
ጋናዊው አቡበከር ታሂሩ ለክብረወሰኑ በአንድ ደቂቃ 19 ዛፎችን ማቀፉም ተነግሯል
ክብረወሰን የመስበር ሙከራውን በረመዳን ጾም ወቅት ማካሄዱ ፈታኝ አድርጎበት እንደበረ ተናግሯል
የተፈጥሮ ጉዳዮች ማህበራዊ አንቂ እና የስነ ደን ተማሪ የሆነው ጋናዊው አቡበከር ታሂሩ በአንድ ሰዓት ውስጥ በርካታ ዛፎችን በማቀፍ አዲስ የዓለም ክብረ ወሰን አስመዝግቧል።
አቡበከር ታሂሩ የተባለው የ29 ዓመቱ ጋናዊ በአንድ ሰዓት ውስጥ በአጠቃላይ 1 ሺህ 123 ዛፎችን ያቀፈ ሲሆን፤ በአንድ ደቂቃ ውስጥም በአማካይ 19 ዛፎችን ማቀፍ ማቸሉ ነው የተነገረው።
በጋና ገጠራማ አካባቢ በሆነችው ቴፓ ያደገው አቡበከር፤ በአርሶ አደር ቤተሰቦች መካከል ማደጉ ለተፈጥሮ ልዩ ፍቅር እንዲኖረው እንዳደረገው ይናገራል።
አቡበከር በስ ደን (ፎረስተሪ) የመጀመሪያ ዲግሪውን በጋና ታዋቂ ዩኒቨርሰቲ ውስጥ ካጠናቀቀ በኋላ በዚሁ የስነ ደን ትምህርት ሁለተኛ ዲግሪውን ለመማር ወደ አሜሪካ ማቅናቱም ነው የተነገረው።
አዲስ ክብረወሰን የማስመዝገብ ሙከራውን ያካሄደውን አሁን በሚገኝባት ሀገረ አሜሪካ ሲሆን፤ ክብረወሰኑን ያመስዘገበውም በአላባማ ውስጥ በሚገኘው ቱስኪጊ ብሄራዊ ደን ውስጥ ነው።
በዚህም አቡበከር ዛፎቹን በሁለት እጆቹ ጥብቅ እያደረገ ሲያቅፍ የነበረ ሲሆን፤ በሙከራው ወቅትም አንድን ዛፍ ደግሞ ማቀፍ አንደማይቻል እና በሚያቅፍበት ጊዜ በዛፎቹ ላይ ጉዳት ካደረሰም ሙከራውን እንደሚያስርዘው ቅድመ ሁኔታ ተቀምጦለት ነበር።
አቡበከር ስለ ዛፍ ማቀፍ ክብረ ወሰኑ ሲናገር፤ “በጣም ከባዱ ነገር በዛፎቹ መካከል የሚደረገው ምልልስ እንዲሁም እያንዳንዱ ዛፍ በተቀመጠው መስፈርት መሰረት መታቀፉን ማረጋገጥ ነበር” ብሏል።
ክብረወሰን የመስበር ሙከራውን የበለጠ ከባድ አድርጎበት የነበረው ሌላኛው ነገር ደግሞ የረመዳን ወቅት መሆኑ እና በመሃል ውሃ መጠጣት አለመቻሉ እንደሆነም አቡበከር ተናግሯል።
ያም ሆኖ አቡበከር ክብረወሰን የመስበር ሙከራውን ያሳከ ሲሆን፤ በየሶስት ሰከንድ ልዩነት አንድ ዛፍ በማቀፍ በአጠቃላይ 700 ዛፎችን በአንድ ሰዓት ውስጥ ማቀፍ አቡበከርን የክብወሰን ባለቤት ለመሆን በቂው ነበር።
ሆኖም ግን ጋናዊው አቡበከር በአንድ ደቂቃ በአማካኝ 19 ዛፎችን በማቀፍ በአጠቃላይ በአንድ ሰዓት ውስጥ 1 ሺህ 123 ዛፎችን በማቀፍ ክብረወሰኑን የግሉ አድርጓል።