ስፖርት
አትሌት መዲና ኢሳ ከ20 አመት በታች የ5 ሺህ ሜትር የሩጫ ውድድር ክብረወሰን ሰበረች
አትሌቷ ባለፈው አመት በራሷ የተያዘውን ክብረወሰን በማሻሻል ነው ያሸነፈችው
አዲዳስ ባዘጋጀው “አዲዜሮ” አመታዊ ውድድር በወንዶቹ ዮሚፍ ቀጀልቻ ማሸነፍ ችሏል
ኢትዮጵያዊቷ አትሌት መዲና ኢሳ በ5 ሺህ ሜትር ከ20 አመት በታች ውድድር ክብረወሰን በመስበር አሸነፈች።
ትጥቅ አምራች ኩባንያው አዲዳስ “አዲዜሮ” የተሰኘ ውድድሩን ለአራተኛ ጊዜ በዛሬው እለት በጀርመን አካሂዷል።
በዚህም ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በሁለቱም ጾታ አሸንፈዋል።
ባለፈው አመት ክብረወሰን በመስበር ያሸነፈችው አትሌት መዲና ኢሳ በዛሬው እለትም የራሷን ክብረወሰን በማሻሻል አሸንፋለች።
የ19 አመቷ አትሌት የ5 ኪሎሜትር ውድድሩን ለማጠናቀቅ 14 ደቂቃ ከ38 ሰከንድ ፈጅቶባታል።
መልክናት ውዱ እና ፎቲየን ተስፋይ 2ኛ እና ሶስተኛ በመሆን ተከታትለው ገብተዋል።
በወንዶች አትሌት ዮሚፍ ቀጀልቻ የ5 ሺ ሜትር ውድድሩን በ13 ደቂቃ በመግባት አሸንፏል።
አትሌት ይሁኔ አዲሱ ዮሚፍን ተከትሎ ሁለተኛ ደረጃን ይዞ ማጠናቀቅ ችሏል።
“አዲዜሮ” አዲዳስ የሚያዘጋጀውና የኩባንያው ዋና መቀመጫ በሆነችው የጀርመን ሄትዞቪኖሃህ ከተማ በየአመቱ ሚያዚያ ወር የሚካሄድ ውድድር ነው።