ስምንት የዓለማችን ሀገራት ብቻ 13 ሚሊዮን የተማሩ ዜጎች ወደ ተለያዩ ሀገራት መፍለሳቸው ተገልጿል
የተማሩ ሰዎች ፍልሰት የበዛባቸው ሀገራት እነማን ናቸው?
የሰው ልጆች ፍልሰት ተፈጥሯዊ እና በፍላጎት መሰረት የሚካሄድ ሲሆን ህጋዊ እና በመረጃ ላይ የተመሰረተ ፍልሰት ይበረታታል፡፡
ሀገራት የተለያዩ ፍላጎቶቻቸውን ለማሟላት ሲሉ የሌሎች ሀገራት ዜጎች እንዲጎበኟቸው ማበረታቻዎችን ይሰጣሉ፡፡
በተለይም የሰለጠነ የሰው ሀይል ፍላጎትን ለማሟላት የቪዛ አገልግሎቶችን ቀልጣፋ እና ቀላል በማድረግ ይታወቃሉ፡፡
የዓለም ባንክ ባወጣው መረጃ መሰረት የሰለጠኑ ሕንዳዊያን ባለሙያዎች ወደ ተለያዩ ሀገራት በመፍለስ ቀዳሚ መሆናቸውን ጠቅሷል፡፡
ከሕንድ በመቀጠል ጎረቤቷ ቻይና እና ፊሊፒንስ ሁለተኛ እና ሶስተኛ ደረጃን የያዙ ሀገራት ሲሆኑ ከአውሮፓ ደግሞ ጀርመን፣ ዩኬ እና ፖላንድም የሰለጠኑ ዜጎቻቸው ወደ ተለያዩ ሀገራት በብዛት ከሚሰደዱባቸው ሀገራት መካከል ተጠቅሰዋል፡፡
ሩሲያ እና ሜክሲኮም የተማሩ ዜጎች ወደ ሌሎች ሀገራት በብዛት ከሚሰደዱባቸው ሀገራት መካከል የተጠቀሱ ሲሆን የተሻለ ክፍያ መፈለግ፣ የፖለቲካ ስርዓት አለመመቸት እና መሰል ጉዳዮች ደግሞየተማሩ ሰዎች እንዲሰደዱ ከሚያደርጉ ምክንያቶች መካከል ተጠቃሽ ናቸው፡፡