በጎበዝ አለቃ የተማረረችው ናይጄሪያ ለዜጎቿ የጦር መሳሪያ ልታስታጥቅ ነው
ናይጄሪያ ከዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰችው በሰሜናዊ የሀገሪቱ ክፍል ዜጎችን የሚያግቱ ሽፍቶች መብዛታቸውን ተከትሎ ነው
ዛምፋራ የተሰኘችው ክልል ዜጎች በሞተር የሚንቀሳቀሱ ሰዎችን ካዩ እንዲገድሉ ፈቃድ ሰጥታለች
በጎበዝ አለቃ የተማረረችው ናይጄሪያ ለዜጎቿ የጦር መሳሪያ ልታስታጥቅ ነው።
አፍሪካን በህዝብ ብዛት እና በሀብት የምትመራው ናይጄሪያ በተለይም በሰሜናዊ የሀገሪቱ ክፍል ዜጎችን በሚያግቱ እና ገንዘብ በሚጠይቁ ሽፍቶች ተማራለች።
የሄንን ህገወጥ እንቅስቃሴ ለማስቆም ስትልም ዜጎች ራሳቸውን እንዲጠብቁ የጦር መሳሪያ ልታስታጥቅ እንደሆነ ተገልጿል።
ምዕራብ አፍሪካዊቷ ናይጀሪያ በተለይም ዛምፋራ የጠሰኘችው ክልል ዜጎች ከአጋቾች እና ጉልበተኞች የሚደርስባቸውን ጥቃት እንዲመክቱ በሚል በነፍስ ወከፍ የጦር መሳሪያ ለማስታጠቅ መወሰኗን ቢቢሲ ዘግቧል።
የዛምፋራ አስተዳዳሪ ለቢቢሲ እንዳሉት በክልሉ አጋቾች መብዛታቸውን ተከትሎ ለዜጎች ያለ ሰልጠና በመቶዎች የሚቆጠሩ የጦር ማሰሪያዎችን እንደሚያስታጥቁ ገልጿል።
ከዚህ በተጨማሪም የጦር መሳሪያ መግዛት የሚችሉ ዜጎች ደግሞ እንዲታጠቁ የተፈቀደላቸቀው ሲሆን፤ ከዜጎች የሚጠበቀው የጦር ማሳሪያቸውን ማስመዝገብ ብቻ መሆኑንም አስተዳዳሪው ተናግረዋል።
ዛምፋራ ክልል የሞተር ተሽከርካሪዎችን እና የነዳጅ ግዢን ለጊዜው ያገደች ሲሆን፤ ዜጎች በሞተር ሳይክል ሲንቀሳቀሱ ካዩ ሞተረኛውን እንዲተኩሱበት እና እንዲገድሉ ፈቃድ መስጠታቸውንም ዘገባው አክሏል።
በሰሜናዊ ናይጀሪያ ዜጎችን እያገቱ የማስለቀቂያ ገንዘብ መጠየቅ እየጨመረ የመጣ ሲሆን በተለይም በገጠር አካባቢ ጉዳዩ አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል።
አጋቾቹ በገጠር ያሉ ትምህርት ቤቶችን፣ ከክልል ክልል ተጓዥ መንገደኞችን እና ሌሎች ገንዘብ ያስገኛሉ ተብለው የሚገመቱ ሰዎችን ኢላማ ያደርጋሉ።