ደቡብ ሱዳን ሁሉንም ትምህርት ቤቶች ዘጋች
ሀገሪቱ ትምህርት ቤቶቿን የዘጋችው በሙቀት ምክንያት ነው
በደቡብ ሱዳን አማከኝ የሙቀት መጠኑ 45 ድግሪ ሆኗል
ደቡብ ሱዳን ሁሉንም ትምህርት ቤቶች ዘጋች፡፡
ጎረቤት ሀገር ደቡብ ሱዳን ባጋጠማት ከፍተኛ የሙቀት መጨመር ምክንያት ለሁለት ሳምንታት ሁሉንም ትምህርት ቤቶች ዘግታለች፡፡
ሀገሪቱ ከዛሬ ጀምሮ ለሁለት ሳምንታት ትምህርት ቤቶች እንዲዘጉ የወሰነችው የሀገሪቱ አማካኝ ሙቀት መጠን 45 ድግሪ በመድረሱ ነው ተብሏል፡፡
የደቡብ ሱዳን ትምህርት እና ጤና ሚኒስትሮች ባወጡት መግለጫ ህጻናት ልጆቻቸውን ከጸሀይ ሙቀት እንዲጠብቁ አሳስበዋል፡፡
ትምህርት ቤቶቹ ለሁለት ሳምንታት ይዘጋሉ ከመባሉ ባለፈ ተጨማሪ መረጃ ተቋማት ያላሳወቁ ሲሆን ትምህርት ቤቶቹ ለተጨማሪ ቀናት ሊዘጉ እንደሚችሉም ተገምቷል፡፡
ተቋማቱ ትምህርት ቤቶቹ እንዲዘጉ የተላለፈውን ውሳኔ ጥሰው የተገኙ ትምህርት ቤቶች ፈቃዳቸው ከመሰረዝ ጀምሮ ተጨማሪ ቅጣት ይጠብቃቸዋልም ተብሏል፡፡
ደቡብ ሱዳን 200 ወታደሮቿ ስልጠና ላይ እያሉ እንደሞቱባት ገለጸች
ደቡብ ሱዳን በአየር ንብረት ለውጥ እየተፈተኑ ካሉ የዓለማችን ሀገራት መካከል አንዷ ስትሆን የሙቀት መጨመር የተለመደ ቢሆንም ከ40 ድግሪ ሴንቲግሬድ አልፎ እንደማያውቅ ቪኦኤ ዘግቧል፡፡
ድርቅ እና በውሃ መጥለቅለቅ ከእርስ በርስ ጦርነት ባለፈ የሀገሪቱ ተጨማሪ ችግር ሲሆን ለደቡብ ሱዳነወዊያን ህይወት በፈተና የተሞላ እንዲሆን እንዳደረገው ተገልጿል፡፡
እንደ ዓለም አቀፉ የምግብ ፕሮግራም ሪፖርት ከሆነ ደቡብ ሱዳን የሰብዓዊ ቀውስ የቀጠለባት ሀገር ስትሆን 810 ሺህ ዜጎች አስቸኳይ የምግብ እርዳታ ያስፈልጋቸዋልም ተብሏል፡፡