ወደ ከባቢ አየር የሚለቀቀው በካይ ጋዝ መጠን መቼ ወደ ዜሮ ይወርዳል?
ዓለማችን አሁን ላይ ወደ ከባቢ አየር የሚለቀቀው ካርበን ጋዝ መጠን 37 ቢሊዮን ቶን ደርሷል
ቴክኖሎጂዎች ወደ ከባቢ አየር የሚለቀቀውን በካይ ጋዝ መጠን ከ80 በመቶ መቀነስ ይቻላል ተብሏል
ወደ ከባቢ አየር የሚለቀቀው በካይ ጋዝ መጠን መቼ ወደ ዜሮ ይወርዳል?
ዓለማችን ከመቼውም ጊዜ በላይ በአየር ንብረት ለውጥ እየተፈተነች ሲሆን የያዝነው ዓመት ደግሞ ከፍተኛ ሙቀት ተመዝግቦበታል።
ለአየር ንብረት ለውጥ ዋነኛው ምክንያት የሆነው ወደ ከባቢ አየር የሚለቀቀው የካርበን ጋዝ ዋነኛው ሲሆን ይህን ለመቀነስ እና በሂደት ወደ ዜሮ ለማውረድ የ50 ዓመት እቅድ ተነድፏል።
በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጸደቀው ይህ እቅድ በ2030 ወደ ከባቢ አየር የሚለቀቀውን ካርበን ጋዝ በግማሽ የመቀነስ ግብ አስቀምጠዋል።
ከአንድ ወር በኋላ በተባበሩት አረብ ኢምሬት ዱባይ የሚካሄደው የተመድ አየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ለዚህ እቅድ መሳካት የሚረዱ ወሳኝ ስርዓት ይጸድቁበታል ተብሎ ይጠበቃል።
ይሁንና አሁን እየተደረገ ባለው ጥረት ይህን እቅድ ማሳካት አይቻልም የተባለ ሲሆን እቅዱን ለማሳካት ሶስት እጥፍ ጥረት መደረግ እንዳለበት ዓለም አቀፉ የሀይል ኤጀንሲ አስታውቋል።
ዓለማችን አሁን ላይ ወደ ከባቢ አየር የሚለቀቀው ካርበን ጋዝ መጠን 37 ቢሊዮን ቶን ደርሷል ተብሏል።
ቴክኖሎጂዎች ወደ ከባቢ አየር የሚለቀቀውን በካይ ጋዝ መጠን ከ80 በመቶ መቀነስ እንደሚቻል ተገልጿል።