የዓለም ጤና ዋነኛ ስጋት ስለሆነው የዝንጆሮ ፈንጣጣ ወቅታዊ መረጃዎች
የአፍሪካ በሽታ እንደሆነ የሚነገረው የዝንጆሮ ፈንጣጣ በበርካታ ሀገራት በመስፋፋት ለይ ይገኛል
መነሻው ከኮንጎ የሆነው ይህ ወረርሽኝ አዲስ ዝርያ ተከስቶ ከ14 ሺህ በላይ ሰዎችን አጥቅቷል
የዓለም ጤና ዋነኛ ስጋት ስለሆነው የዝንጆሮ ፈንጣጣ ወቅታዊ መረጃዎች
እንደ ዓለም ጤና ድርጅት መረጃ ከሆነ የዝንጆሮ ፈንጣጣ በምዕራብ አፍሪካዊቷ ኮንጎ የተገኘ ሲሆን ቫይረሱ ወደ ጎረቤት ሀገራት በመስፋፋት ላይ ይገኛል፡፡
ይህ በሽታ ከዚህ በፊትም የሚታወቅ ሲሆን በቅርቡ ግን አዲስ የበሽታው ዝርያ በስርጭት መጠኑ ከፍተኛ መሆኑን ተከትሎ የዓለም ጤና ድርጅት የዓለማችን ጠየና ዋነኛ ስጋት መሆኑን አውጇል፡፡
የዝንጆሮ ፈንጣጣ ለመጀመሪያ ጊዜ በ1970 የተለየ ሲሆን ወደ ተለያዩ የዓለማችን ሀገራት ቢሰራጭም ለዓለም ጤና ግን አስጊ ሆኖ አይውቅም ነበር፡፡
ገዳይ ከሆኑ በሽታዎች መካከል አንዱ የሆነው የዝንጆሮ ፈንጣጣ አዲሱ ዝርያ እስካሁን 14 ሺህ ሰዎችን ሲያጠቃ 524 ሰዎችን ገድሏል፡፡
የዝንጆሮ ፈንጣጣ በሽታ በቫይረስ የሚተላለፍ ሲሆን ቫይረሱ ከእንስሳት ወደ ሰዎች ሳይተላለፍ እንዳልቀረ ይታመናል፡፡
በአካላዊ ንኪኪ የሚተላለፈው የዝንጆሮ ፈንጣጣ በሽታ ከሁለት ዓመት በፊት ዓለም አቀፍ ትኩረት የሚያስፈልገው በሽታ ተብሎ በዓለም ጤና ድርጅት ተወስኗል፡፡
ስዊድን፣ ፓኪስታን እና ሌሎችም ሀገራት የዝንጆሮ ፈንጣጣ ለመጀመሪያ ጊዜ ከአፍሪካ ውጪ የተገኘባቸው ሀገራት ናቸው፡፡
የአለም ጤና ድርጅት የዝንጀሮ ፈንጣጣ የህብረተሰብ ጤና ስጋት ሆኗል ሲል ለሁለተኛ ጊዜ አወጀ
አንድ በዝንጆሮ ፈንጣጣ አምጪ ቫይረስ የተጠቃ ሰው የበሽታውን ምልክቶች በሁለት ሳምነታት ውስጥ የሚያሳይ ሲሆን ራስ ምታት፣ የጡንቻ መዛል፣የጀርባ ህመም፣ትኩሳት፣ ከወትሮው የተለየ ላብ ማላብ፣የጉሮሮ ህመም እና የድካም ስሜት ዋነኞቹ የበሽታው ምልክቶች ናቸው፡፡
በዚህ ቫይረስ የተጠቃ ሰው በወቅቱ ህክምና የሚያገኝ ከሆነ ታክሞ የሚድን ሲሆን ተገቢውን ህክምና ያላገኙ የቫይረሱ ተጠቂዎች ህይወታቸውን ሊያጡ ይችላሉ ተብሏል፡፡