የጎግል እናት ኩባንያ አልፋቤት ስራ አስኪያጅ የሆኑት ሰንዳር ስንት ይከፈላቸዋል?
የዓለማችን ከፍተኛ ደመወዝ ተከፋዩ ሰው ማን ነው?
በፈረንጆቹ 1972 በሕንዷ ታሚል ናዱ ግዛት የተወለዱት ሰንዳር ፒቻይ አሁን ላይ ከፍተኛ ደመወዝ ከሚከፈላቸው ሰዎች መካከል ቀዳሚው ናቸው።
የጎግል እናት የሆነው አልፋቤት ኩባንያን በስራ አስኪያጅነት የሚመሩት ሰንዳር የዓለማችን ተጽዕኖ ፈጣሪው ስራ አስኪፓጅም ናቸው።
ለብዙ ወጣቶች አርዓያ ናቸው የሚባልላቸው ሰንዳር ከመካከለኛ የሕንድ ቤተሰብ መገኘታቸው ይገለጿል።
በትምህርት ቤት ጎበዝ ተማሪ እንደነበሩ የሚነገርላቸው ሰንዳር በቴክኖሎጂ ዘርፍ ካሉ የዓለማችን ምሁራን መካከል አንዱ ናቸው።
በፈረንጆቹ 1993 ላይ የመጀመሪያ ድግሪያቸውን ከህንዷ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት አግኝተዋል ተብሏል።
በመቀጠልም የስኮላርሺፕ ትምህርት እድል አግኝተው ወደ አሜሪካው ስታንፎርድ ዩንቨርስቲ በመግባት በሁለተኛ ድግሪ ተመርቀዋል።
ከ2004 ጀምሮም ጎግል ኩባንያን የተቀላቀሉት ሰንዳር የአንድሮይድ ሲስተም አስተዳድር ሆነው ሲያገለግሉ ከቆዩ በኋላ አሁን ላይ የኩባንያው ስራ አስኪያጅ ሆነው በማገልገል ላይ ናቸው።
226 ሚሊዮን ዓመታዊ ደመወዝ የሚከፈላቸው ሰንዳር በበርካታ የዓለማችን የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች ተፈላጊ ሰውም ናቸው።
ሰንዳር የኢለን መስኩ ኤክስ ኩባንያ ዳጎስ ያለ ደመወዝ ቢያቀርብላቸውም ጎግልን አለቅም ብለው ጉርሻውን ውድቅ አድርገዋል።
ጎግል ኩባንያም ለሰንዳር ታማኝነት የ50 ሚሊዮን ዶላር ስጦታ እንዳቀረበላቸው ተገልጿል።