የዓለም ጦር መሳሪያ ዓመታዊ ግዢ ከዓምናው ጋር ሲነጻጸር የ0.7 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል
የዓለም የጦር መሳሪያ ዓመታዊ ግብይት ከ2 ትሪሊየን የአሜሪካ ዶላር ማለፉ ተነግሯል።
የስቶኮልም ዓለም ዓቀፍ ጥናት ኢንስቲትዩት ባወጣው ሪፖርት የዓለም የጦር መሳሪያ ዓመታዊ ግብይት 2 ነጥብ 1 ትሪሊየን የአሜሪካ ዶላር መድረሱን አስታውቋል።
ይህም በዓለም ዓመታዊ የጦር መሳሪያ ግብይት በታሪክ ከፍተኛው ሆኖ መመዝገቡ የተገለጸ ሲሆን፤ የዘንድሮው ከዓምናው ጋር ሲነጻጸር የ0 ነጠብ 7 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል ተብሏል።
የጦር መሳሪያ ግዢ ጭማሪው በዓለም ዓመታዊ ምርት ላይ የ0 ነጥብ 1 በመቶ ቅናሽ እንዲያስመዘግብ ምክንያት እንደሚሆንም የኢንስቲትዩቱ ሪፖርት ያስረዳል።
በፈረንጆቹ 2021 ዓመት በነበረው የጦር መሳሪያ ግዢ አሜሪካ፣ ቻይና፣ ህንድ፣ እንግሊዝ እና ሩሲያ ለጦር መሳሪያ ከፍተኛ ወጪ የሚያወጡ ቀዳሚዎቹ የዓለማችን ሀገራት ናቸው።
እነዚህ ሀገራት 62 በመቶ የዓለማችን ጦር መሳሪያ ዓመታዊ ወጪ ድርሻ እንዳላቸውም በጥናቱ ተገልጿል።
የጦር መሳሪያ ወጪው የጨመረው አሜሪካ በአዲስ መልክ ቀጣዩን ትውልድ መሰረት ያደረጉ የጦር መሳሪያ ቴክኖሎጂዎች ላይ ትኩረት በማድረጓ ነው ተብሏል።
የሩሲያ ዓመታዊ የጦር መሳሪያ ወጪ ከዓምናው ጋር ሲነጻጸር የ2 ነጥብ 9 በመቶ ወይም 65 ነጥብ 9 ቢሊዮን ዶላር መድረሱ በጥናቱ ተጠቁሟል።
የሩሲያ ዓመታዊ የጦር መሳሪያ ከፈረንጆቹ 2016 እስከ 2019 ድረስ በዓለም የነዳጅ ዋጋ መቀነሱን ተከትሎ የጦር መሳሪያ ወጪዋን የቀነሰች ሲሆን አሁን ደግሞ በድጋሚ ወጪው በመጨመር ላይ ትገኛለች።
ከሩሲያ ጋር ጦርነት ውስጥ ያለችው ዩክሬን ዓመታዊ የጦር መሳሪያ ወጪዋን በ72 በመቶ ጭማሪ ማድረጓ ተገልጿል።