በፈረንጆቹ 2021 የአሜሪካ የጦር መሳሪያ ሽያጭ በ21 በመቶ መቀነሱ ተነገረ
በቀደሙት ዓመታት የሀገሪቱ ዓመታዊ የመሳሪያ ሽያጭ 175 ቢሊየን ዶላር ነበር
እየተገባደደ ባለው የአውሮፓውያኑ 2021 አጠቃላይ ሽያጩ ወደ 138 ቢሊየን ዶላር ዝቅ ብሏል
እየተገባደደ ባለው በፈረንጆቹ 2021 የአሜሪካ ዓመታዊ የጦር መሳሪያ ሽያጭ በ21 በመቶ ቅናሽ ማሳየቱን ሪፖርት አመላከተ።
በዓመቱ አሜሪካ በአጠቃላይ ከጦር መሳሪያ ሽያጭ 138 ቢሊየን ዶላር ያገኘጭ ሲሆን ሲሆን ይህም ከዚህ ቀደም ከነበሩ ዓመታ ጋር ሲነጻጸር ዝቅተኛ መሆኑ ተነግሯል።
የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የፈረንጆቹ 2021 ወታደራዊ ሽያጭን የሚያሳይ ሪፖርት ከሰሞኑ ይፋ አድርጓል።
በሪፖርቱም በአጠቃላይ አሜሪካ የ138 ቢሊየን ዶላር ሽያጭ ማከናወኗ ተመላከተ ሲሆን፤ ባለፈው ዓመት ከተከናወነው የ175 ቢሊየን ዶላር ሽያጭ ጋር ሲነጻጸር ከፍተኛ የሆነ ቅናሽ ሳይቷል።
የአሜሪካ አስተዳደር የመሳሪያ ሽያጭ ፖሊሲውን በሰዓዊ መብት ላይ ትኩረት ባደረገ መልኩ ለማስተካከል እየሰራ መሆኑ ለቅናሹ ምክንያት ሊሆን እንደሚችል ተነግሯል።
የአሜሪካ የቀድሞ ፕሬዚዳት ዶናልድ ትራምፕ በመጨረሻወቹ ስልጣን ዘመናቸው የጦር ጀቶችን እና ሚሳኤሎችን ጨምሮ በርካታ የጦር መሳሪያዎች ሽያጭ ማከናወናቸው ይታወሳል።
እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ2020 ብቻ በተካሄዱ የጦር መሳሪያ ሽያጭ ስምመነቶች ውስጥም ጃፓን በ23 ቢሊየን ዶላር የፈፀመችው 63 የ F-35 ተዋጊ ጄቶች ግዢ ተጠቃሽ ነው።
እነዚህ እና ሌሎችም ምክንያቶች እየተገባደደ ባለው የፈረንጆቹ 2021 የአሜሪካ ዓመታ የጦር መሳሪያ ሽያጭ ቅናሽ እንዲያሳይ ማድረጋቸው ተመላክቷል።
የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች በቅርቡ ከአሜሪካ ልትገዛቸው የነበሩ ኤፍ-35 ተዋጊ ጀቶችን እና ሰው አልባ የጦር አውሮፕላኖችን (ድሮኖችን) ግዥ ልታቆም እንደምትችል ማስጠንቀቋ ይታወሳል።