የዓለማችን 10 አስጨናቂ ኤርፖርቶች እነማን ናቸው?
ቪዛ ጋይድ የተሰኘው ዓለም አቀፍ የጉዞ ድርጅት በ53 ሀገራት ያደረገውን የጥናት ውጤቱን ይፋ አድርጓል
በመጠናቀቅ ላይ ያለው 2023 ኤርፖርቶች በሰራተኞች ዓመጽ እና መጥፎ አየር ንብረት የተፈተኑበት እንደነበር ተገልጿል
የዓለማችን 10 አስጨናቂ ኤርፖርቶች እነማን ናቸው?
ቪዛ አድቫይስ የተሰኘው ዓለም አቀፍ የጉዞ ድርጅት እየተጠናቀቀ ባለው 2023 ዓመት የነበሩ የጉዞ እና ጉብኝት ሁነቶችን ይፋ አድርጓል።
ድርጅቱ በ53 ሀገራት ተዘዋውሮ በተያዘው ዓመት ሁለት ጊዜ እና ከዛ በላይ በሁለት አህጉራት ጉብኝት ያደረጉ ከ1 ሺህ 600 በላይ ጎብኚዎችን ያሳተፈ የጥናት ውጤቱን ይፋ አድርጓል።
በዚህ ድርጅት ሪፖርት መሰረት የፈረንጆቹ 2023 ኤርፖርቶች እና አየር መንገዶች በሰራተኞቻቸው አድማ እና የጥቅማጥቅም ጥያቄዎች የተፈተኑበት ዓመት እንደነበር ዩሮ ኒውስ ዘግቧል።
እንዲሁም ሙቀት መጨመር፣ ቅዝቃዜ እና ከባድ አውሎ ንፋስ እና ጎርፍ በርካታ በረራዎችን ያስተጓጎሉበት ዓመትም እንደነበር ተገልጿል።
ይህ በዚህ እንዳለ ጎብኚዎች አስጨናቂ ናቸው ያሏቸውን አየር መንገዶችን ይፋ ያደረጉ ሲሆን በአንደኝነት አስጨናቂው ኤርፖርት የተባለው የለንደኑ ጋትዊክ ኦርፖርት ነው።
ይህ ኤርፖርት በርካታ መንገደኞችን ማስተናገዱ ያስጨንቃልብየተባለ ሲሆን የኤርፖርቱ ስፋትም ሌላኛው ለተጓዦች አመቺ እንዳይሆን አድርጎታል ተብሏል።
የቱርኩ አታቱርክ ኤርፖርት ሁለተኛው አስጨናቂ ኤርፖርት ሲሆን በዓመት ከ60 ሚሊዮን በላይ መንገደኞችን ያስተናግዳል።
በዓመት ከ31 ሚሊዮን በላይ መንገደኞችን ያስተናግዳል የተባለው ሌላኛው አስጨናቂ ኤርፖርት ደግሞ የጀርመኑ ሙኒክ ኤርፖርት ነው።
የአሜሪካዎቹ ዴንቨር፣ ሎስ አንጀለስ እና ዳላስ ኤርፖርቶች አስጨናቂ ኤርፖርቶች ተብለው ከተለዩት መካከል ዋነኞቹ ናቸው።
የብሪታንያው ሂትሮው እና የጣልያኑ ሮም ፉሚሲኖ ኤርፖርቶች በዓለም አቀፍ መንገደኞች አስተያየት መሰረት በአስጨናቂነት ተይዘዋል።
ዱባይ፣ ቶኪዮ፣ ለንደን፣ ዳላስ እና ኢስታምቡል ከተሞች በ2023 ብዙ በረራዎች የተደረጉባቸው ምርጥ አምስት ከተሞች ናቸው።