በቱርክ የሚፈለገው የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ወንድ ልጅ ምን ወንጀል ሰርቶ ይሆን?
የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ወንድ ልጅ የሆነው መሀመድ ሀሰን በኢስታምቡል ፖሊስ የእስር ማዘዣ ወጥቶበታል
በኢስታምቡል ከተማ ይኖር የነበረው የፕሬዝዳንቱ ልጅ የበረራ እገዳ ቢጣልበትም ወደ ሞቃዲሾ አምልጧል ተብሏል
በቱርክ የሚፈለገው የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ወንድ ልጅ ምን ወንጀል ሰርቶ ይሆን?
የጎረቤት ሀገር ሶማሊያ ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሀመድ ወንድ ልጅ የሆነው መሀመድ በቱርኳ የኢኮኖሚ መዲና ኢስታምቡል ከተማ ይኖር ነበር ተብሏል፡፡
ከሳምንታት በፊት በዚችው ከተማ ንብረትነቱ በቱርክ የሶማሊያ ኢምባሲ የሆነ ተሽከርካሪ እያሽከረከረ እያለ በሞተር ሳይክል እየተጓዘ የነበረ ሰውን እንደገጨ ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
እንደዘገባው ከሆነ ይህ መተረኛ ሰው በደረሰበት የትራፊክ አደጋ ህይወቱ ያለፈ ሲሆን የሶማሊ ፕሬዝዳንት ልጅም በዚህ የሰው መግደል ወንጀል ይፈለጋል፡፡
የከተማው ፖሊስ የፕሬዝዳንቱን ልጅ አስሮ የነበረ ቢሆንም ከትንሽ ጊዜ እስር በኋላ ባልታወቀ ምክንያት ከእስር ሊፈታ መፈታቱ ተገልጿል፡፡
የኢስታምቡል ፖሊስም በዚህ ግለሰብ ላይ ከሀገር እንዳይወጣ የበረራ እገዳ የተላለፈበት ቢሆንም ባልታወቀ ምክንያት ግን ቱርክን በመልቀቅ ወደ ሞቃዲሾ እንደበረረ በዘገባው ላይ ተጠቅሷል፡፡
በሶማሊያ ላይ ተጥሎ የነበረው የጦር መሳሪያ ማዕቀብ ከ30 አመታት በኋላ ተነሳ
በፕሬዝዳንቱ ልጅ የተገጨው ይህ ቱርካዊ የሁለት ልጆች አባት የሆነ የ38 ዓመት ሰው እንደሆነም ተገልጿል፡፡
ተጠርጣሪው ከቱርክ ማምለጡን ተከትሎ የኢስታምቡል ፖሊስ የትራፊክ አደጋው ሲደርስ የሚያሳየውን ተንቀሳቃሽ ምስል በማህበራዊ ትስስር ገጾች ላይ አጋርቷል፡፡
የፕሬዝዳንቱ ልጅ እስካሁን ስለሁኔታው አስተያየት ከመስጠት የተቆጠበ ሲሆን ቱርክ ይህ ተፈላጊ ሰው ተላልፎ እንዲሰጣት ዓለም አቀፍ የእስር ማዘዣ አውጥታለች ተብሏል፡፡
ቱርክ እና ሶማሊያ በየጊዜው እያደገ የመጣ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ያላቸው ሲሆን በተለይም ቱርክ ወታደራዊ ስልጠናዎችን እና የመሰረተ ልማት ግንባታዎች ስልጠና ሰጥታለች፡፡