በወሲባዊ ጥቃት ወንጀል ተከሶ ፍርደኛ ለነበረ ግለሰብ ይቅርታ ያደረጉ ፕሬዝደንት ስልጣን ለቀቁ
ኖቫክ ፕሬዝደንታዊ ይቅርታውን ያደረጉት ባለፈው ሚያዝያ ወር ቢሆንም መነጋገሪያ የሆነው ግን ባለፉት ቀናት ነው
ግለሰቡ በልጆች ማቆያው ኃላፊ ጥቃት የደረሰባቸው ሰለባዎች እንዳይናገሩ ጫና በማሳደር ጥፋተኛ ተብሎ በ2018 የሶስት አመት እስር ተፈርዶበት ነበር
በወሲባዊ ጥቃት ወንጀል ተከሶ ፍርደኛ ለነበረ ግለሰብ ይቅርታ ያደረጉ ፕሬዝደንት ስልጣን ለቀቁ።
በመንግስት በሚተዳደር የልጆች ማቆያ ውስጥ በተፈጸመ የህጻናት ወሲባዊ ብዝበዛ ተከሶ ጥፋተኛ ለተባለ ግለሰብ ይቅርታ ያደረጉት የሀንጋሪ ፕሬዝደንት ከስልጣናቸውን ለመልቀቅ ተገድደዋል።
የ46 አመቷ ካታሊን ኖቫክ ፕሬዝደንታዊ ይቅርታውን ያደረጉት ባለፈው ሚያዝያ ወር ቢሆንም መነጋገሪያ የሆነው ግን ባለፉት ቀናት መሆኑን ስካይ ኒውስ ዘግቧል።
በመላ ሀገሪቱ ተቃውሞ መነሳቱን ተከትሎ ፕሬዝደንት ኖቫክ "ብዙ ህዝብን ያስገረመ እና የረበሸ ይቅርታ አድርጌአለሁ። ስህተት ሰርቻለሁ" ብለዋል።ኖቫክ የሀንጋሪው ቀኝ ዘመም ጠቅላይ ሚኒስትር ቪክተር ኦርባን የቅርብ አጋር ናቸው።
ኖቫክ በፈረንጆቹ 2022 ስልጣን ሲይዙ በታሪክ የመጀመሪያዋ ሴት ፕሬዝዳንት መሆን ችለው ነበር።
ግለሰቡ በልጆች ማቆያው ኃላፊ ጥቃት የደረሰባቸው ሰለባዎች እንዳይናገሩ ጫና በማሳደር ጥፋተኛ ተብሎ በ2018 የሶስት አመት እስር ተፈርዶበት ነበር።
የማቆያው ኃላፊ ከ2004 እስከ 2016 ድረስ በ10 ህጻናት ላይ ጥቃት በማድረስ 10 አመታት ታስረዋል።
ይህ ጉዳይ የፕሬዝዳንቷን ይቅርታ አጽድቀዋል የተባሉትን የቀድሞ የሀገሪቱን የፍትህ ሚኒስትር ጁቲት ቫርጋንም ተጠያቂ አድርጓል።
ቫርጋ በፌስቡክ ገጻቸው ከፖርላማ አባልነታቸው እንደሚለቁ እና በህዝባዊ ኃላፊነት ላይ እንደማይሳተፉ ተናግረዋል።
ከ2020 ጀምሮ ስልጣን የተቆጣጠረው የኖቫክ ፊደዝ ፖርቲ መሪ ኦርባን የቀረበባቸውን የድምጽ ማጭበርበር እና የሚዲያ ቁጥጥር ክስ ማጣጣላቸውን ተከትሎ አለመረጋጋት ውስጥ ገብቷል።
የኦርባን ጠንካራ ደጋፊ የሆኑት ኖቫክ የባህላዊ ቤተሰባዊ እሴቶችን እና የህጻናት መብት ጥበቃ አራማጅ ናቸው።