ኢንዱስትሪና የካርበን ልቀት በኮፕ28
በ2023 ከኢንዱስትሪዎች የሚለቀቀው ካርበን ዳይ ኦክሳይድ 37 ጊጋ ቶን እንደሚሆን ይገመታል
28ኛው የአለም የአየር ንብረት ለውጥ ነገም ቀጥሎ ሲካሄድ የኢንዱስትሪዎች የበካይ ጋዝ ልቀት ይመከርበታል
ከኢንዱስትሪዎች የሚለቀቅ በካይ ጋዝ የአየር ንብረት ለውጥን ማስከተል ከጀመረ አመታት ተቆጥረዋል።
ከኢንዱስትሪ አቢዮት የጀመረው ብክለት እንዲቀንስ ሀገራትና የግዙፍ ኢንዱስትሪዎች መሪዎች በተደጋጋሚ ቃል ቢገቡም ተፈጻሚ ሲሆን አይታይም።
በ2022 ከኢንዱስትሪዎች ወደ ከባቢ አየር የተለቀቀው ካርበን ዳይ ኦክሳይድ 36 ነጥብ 8 ጊጋ ቶን እንደነበር የግሎባል ካርበን በጀት ፕሮጀክት መረጃ ያሳያል።
በ2023ም 37 ነጥብ 2 ጊጋ ቶን ካርበን ከኢንዱስትሪዎች እንደሚለቀቅ ይገመታል።
በየአመቱ ከመቀነስ ይልቅ ጭማሪ የሚያሳየው የኢንዱስትሪዎች የበካይ ጋዝ ልቀት አሳሳቢ ሆኗል።
28ኛው የአለም የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ነገም በዱባይ ቀጥሎ ሲካሄድ ይሄው ጉዳይ በስፋት ይመከርበታል። የጉባኤውን ዝርዝር ጉዳዮች ይመልከቱ፦