የዓለም ንግድ ድርጅት “አረብ ኢሚሬትስ የዘላቂነት ታሪክ እየሰራች ነው” አለ
የድርጅቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር: የዓለም ንግድ ድርጅት በኮፕ 28 ለመጀመሪያ ጊዜ እንደሚሳተፉ ገልጸዋል
የአለም ንግድ ድርጅት አረብ ኤምሬትሰ በአለም አቀፍ ንግድ ውስጥ የተጫወተችውን የመሪነት ሚናና የንግድ ልውውጥ ቀጣይነት አድንቋል
የዓለም ንግድ ድርጅት “አረብ ኢሚሬትስ የዘላቂነት ታሪክ እየሰራች ነው” ሲል አደነቀ።
የድርጅቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዣን ማሪ ቢዩጋም በጄኔቫ ከአል ዐይን ኒውስ ጋር ባደረጉት ልዩ ቃለ ምልልስ፣ አረብ ኤምሬትስ የዓለም ንግድ ድርጅት የሚኒስትሮች ስብሰባ በሚቀጥለው የካቲት በአቡ ዳቢ በማዘጋጀት የመሪነት ሚና እየተጫወተች መሆኑን አረጋግጠዋል።
ቢዩጋም አክለውም አቡዳቢ የምታዘጋጀው የዓለም ንግድ ድርጅት የሚኒስትሮች ስብሰባ በጣም ስለ ንግድ ፣ ዘላቂነት እና አካባቢ መልእክትቶች ከሚንጸባረቁበት ወሳኝ ከሆነው ኮፕ 28 ቀጥሎ የሚካሄድ መሆኑን ጠቅሰዋል።
ይህም አረብ ኢምሬትስ በ28ኛ የተመድ የዐየር ንብረት ለውጥ ጉባዔ (ኮፕ28) ላይ ለማስተላለፈቸው የፈለገችውን መልእክት እና በዓለም ንግድ ጉባዔድርጅት መካካል ያለውን ቁርኝት ያሳያል ብለዋል።
አረብ ኢምሬትስ በኮ28 ፕሬዘዳንትነቷ ታሪክ እየሰራች ነው ያሉት ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ፤ ምክንያ ደግሞ በዔር ንብረት ጉባዔ ላይ በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ለንግድ የተሰጠ ቀን እንዲኖር በማድረጓ ነው ብለዋል።
ከዚህ ቀደም በተደረጉ የተመድ የዐየር ንብረት ለውጥ ጉባዔ ላይ ስለ ንግድ ተነስቶ እንደማያውቅ ያስታወቁት ቢዩጋም፤ ይህም ክፍተትን ፈጥሮ ቆይቷል፤ ምክንያ ደግሞ የዐየር ንብረት ለውጥን በመቀነስ እና በመከላከል ረደግ ንግድ የራሱን ሚና ስለሚጫወት ነው ብለዋል።
የዓለም ንግድ ድርጅት በዱባይ በሚካሄደው ኮፕ28 ላይ በተሰየመው የንግድ ቀን ላይ ን ከዩንክታድ እና ከአለም ኢኮኖሚክ ፎረም ጋር በመሆን በልዩ ኮሚቴ በኩል እንደሚሳተፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ ገልጸዋል።
በኮፕ28 ላይ የዓለም ንግድ ድርጅት ዋና ዳይሬክተር በተገኙበት ንግድን የአየር ንብረት ጉባኤ አስፈላጊ አካል ለማድረግ እንደሚሰራም አስታውቀዋል።